Wednesday 3 May 2017

ለነፃነታችን በመርህ እንታገል!!

ወያኔዎች ስለሚፈፅሙት ወንጀል ማውራት ብቻ መፍትሔ አይሆንም፡፡ የችግሩን ፈጣሪ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ግለሰብዓዊ የመረጃ ጥቃት መፈፅም አለብን፡፡ ፌስቡክ ላይ ሆነን ወያኔዎችን በመረጃ ከማጥቃ ውጭ ለነፃነት አስተዋጽኦ ማድረግ አይቻልም፡፡ ፌስቡክ ላይ ወያኔዎች የሚጠቁት በመረጃ ጦርነት ነው፡፡ ወንጀሎችን ብቻ ማውራት መፍትሔ አይሆንም፡፡ ወንጀለኞችን በግለስብ ደረጃ ማጥቃት አለብን፡፡
ከቻልክ በመሳሪያ መታገል ነው፡፡ ካልቻልክ ወያኔን በመረጃ ማጥቃት ነው፡፡ መረጃዎች ኃይል ናቸው እንጠቀምባቸው፡፡ ወያኔዎች እኮ ማህበራዊ ሚዲያውን እንደሚፈሩት በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ ብዙ ብር አውጥተው የመረጃ ሰራዊት አደራጅተው እየዘመቱብን ነው፡፡ ለምን እኛስ አናደርገውም? 
ወያኔ የግለሰቦች ስብስብ ነው፡፡ በሚመሩት ግለሰቦች ላይ የመረጃ ዘመቻ ብናደርግ የኃይል ሚዛን እናዛባለን፡፡ ከዚህ ውጭ ፌስቦክ ላይ ተኩሰን አንገላቸው፡፡
የትጥቅ ትግሉ እንዲፋጠን የኃይል ሚዛን መዛባት አለበት፡፡ የኃይል ሚዛን የሚዛባው በመረጃ ጥቃት ነው፡፡ መከፋፈል የሚፈጠረው በመረጃ ጥቃት ነው፡፡ መፈረካከስ እና ብተና የሚፈጠረው በመረጃ ጥቃት ነው፡፡
ትግል መርህ ነው በመርህ እንተባበር፡፡ መርሆዎቻችን ደግሞ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት አስጠብቀን፤ ዲሞክራሲያዊ የመንግሥት ስረዓት መፍጠር ነው፡፡ ስለዚህ እየተናበብን በተጠና መልኩ የወያኔን ተላላኪዎች ግላዊ መረጃዎች አደባባይ በማውጣት የራስ መተማመናቸውን በመሸርሸር እንዲበረከኩ ማድረግ እንችላለን፡፡ እንዲ ሸማቀቁ፣ እንዲያፈገፍጉ እና እንዲበተኑ እናደርጋለን፡፡
በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን የትጥቅ ትግል ፌስብክ ላይ ሆነን መደገፊ የምንችለው በመረጃ ዘመቻ ነው፡፡ "ወያኔ እከሌን ገደለው" እያሉ ማውራት ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ማነው የገደለው? ትዕዛዝ የሰጠው ማነው? የግልና የቤተሰብ ማህበራዊ ህይወቱ ምን ይመስላል? ከወያኔጋ ያለው የጥቅም ትስስሩ ምን ይመስላል? ብለን ወንጀላቸውን አደባባይ ማውጣት አለብን፡፡ ከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ ይፈጥራል፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ነው ማንም ከስነልቦና ጫና አያመልጥም፡፡
ለህዝብ ጠላቶቹን በመረጃ ማሳወቃችን እንዲያገላቸው እና እንዲታገላቸው ያደርጋል፡፡ለምሳሌ ባህር ዳር የሚገለው እና የሚያስገድለው እኮ አባይ ፀሀዬ አይደለም፡፡ የሱን ትዛዝ ተቀብለው የሚፈፅሙት ላይ እናተኩር፡፡ ተባባሪዎች አሉ፤ እነሱ እነማን ናቸው? ኑሯቸው እንዴት ነው? በምንድን ነው የሚተዳደሩት? ብለን መጠየቅ እና መልስ መሻት ያስፈልጋል፡፡ 
ብዙዎቹ ወያኔዎች ሴሰኞች ናቸው የት ነው የሚሴስኑት? ሚስት ታወቃለች? ልጆችስ? ማንን ነው ያስገደሉት? የሟች ቤተሰቦች የልጃቸውን ገዳይ በግለሰብ ደረጃ ያውቃሉ ወይ? መልስ ልንስጣቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
በህዝብ ላይ በቀጥታ ጥቃት በሚፈፅሙት ላይ መዝመት አለብን፡፡ የታችኛውን የወያኔ ፈፃሚዎች በማንበርከክ የላይኛውን ወያኔ ማንሳ፣ፍና ለጥቃት ማጋለጥ ይቻላል፡፡ እስከ መጨረሻው ለማሰናበት የነፃነት ኃይሎች አሉ፡፡ እና በመረጃ ጦርነት እናግዛቸው፡፡
ለነፃነታችን በመርህ እንታገል!!

No comments:

Post a Comment