Sunday 24 July 2016

(Amanye Paramera)
ወደድንም ጠላንም ወልቃይት; ራያ እና መተከል በአማራ መንግስት መተዳደራቸዉ አይቀሬ ነዉ:: በታሪክም ሆነ በደም ሌላ ማንነት ተሸክመዉ አያቁም; በግድ የተጫነባቸዉን የሚከረፋ ካባ የሚጥሉበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም:: ማንነታችን በግድ ለመድፈቅ የህዉሐት ተንኮል እና ስነ-ኦነጋዊ አቅጣጫ ማስቀየሪያዋ መቼም አይቻላትም:: እስከአሁንም ''ከመጥፋት ላላመለጠችዋ ሐገር'' ብለን ነበር:: አሁን አማራ ብቻ ሁነናል; ስለአማራ ብቻ ማሰብ ጀምረናል; የእኛን ታሪክ ብቻ መቆፈር ጀምረናል; ማንም ባንዳ ከእኛ ጋ እኩል በወል መጠሪያችን '' የኢትዬጵያ ታሪክ'' እያለ በአለም አደባባይ የሚኩራራበት ታሪክ የእኛ ብቻ መሆኑን አረጋግጠናል:: አማራ ብቻዉን ሙሉ ነዉ; ትልቅ አገር ነዉ; ትልቅ ታሪክ; የአለማችን ምሑራን ለማወቅ የሚጓጉለት ምጡቅ እዉቀት በየገዳማቱ አሉት; አማራ ብቻዉን እንደ እስራኤል አስፈሪ እንደ ግሪክ ባለታሪክ እንደ ጀርመን ባለግርማሞገስ መሆን ይችላል!! እናንተ ኦነጋዉያን የወልቃይትን ጥያቄ በሸገር ለመሸፈን የምትቆምሩ የህዉሓት ፈረሶች አደለም ሸገር ወለጋ ርስት እንደሌላችሑ ለማወቅ የቆማችሑበትን መሬት ትንሽ ቆፈር ብታደርጉት ''አማራ አማራ'' ይሸታችሗል::
:
እመኑኝ አማራ ብቻዉን ሙሉ ነዉ!!

ከሃዲውን አንከዳውም ግን እናሰወግደዋለን!

ከሃዲውን አንከዳውም ግን እናሰወግደዋለን!
ወዮልህ ነብር አየኝ በል!!
አለኸኝ አቻምየለህ ይባላል የወልቃይት አማራ ማንነት ጠያቂ ኮሚቴ ውስጥ ይሳተፍ የነበረ አባልም ነበር። አሁን ግን ለትግሬ በገንዘብ ተገዝቶ ልጆቻችንን አሳልፎ እየሰጠ አና የሀሰት ምስክርነት እናቱን ጨምሮ ወ/ሮ ፀጋዬ መከተ እና አጎቱ ሆነው እየሰጡ ይገኛሉ ። ከዛም ባለፈ የወልቃይትን ወጣቶች ለማሳፈን ከትግሬዎች ጋር እየሰራ ይገኛል።
የተከበረው አማራ ባንዳነትን ፈፅሞ ይፀየፋል! ይህ ሆዳም ባንዳ ዋጋው ይሰጠው!!
በአስቸኳይ ከመንገዳችን ገለል ሊደረግ ይገባል!!
# አማራ ተጋድሎ
# ወልቃይት_ከሌለ_የለም_አማራነት !!
ከዞማAdjama Dejene's photo.

Thursday 14 July 2016

ሰበር ዜና. . . . . የህወሃት ብሐራዊ መረጃ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብቶአል።

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የእስራኤል ከፍተኛ ባልስልጣኖችን ለማዉጣት ከእስራኤል ሔለኒክ አየር ሐይል የልዩ ሐይል ( SPECIAL FORCE ) አባላትን የያዘ የጦር ጀቶችና አፓቼ ሄሊኮፍተሮች ( Apache Helicopters ) ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የተጠየቀዉ የወያኔዉ ብሔራዊ ደህንነት አመጽ በተቀሰቀሰባቸዉ የጎንደር አካባቢዎች ሰላም ሰፍሮዋል የሚል የተዛባ ማስተባበያ እየሰጠ ይገኛል።
ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ መንስኤ የሆነዉ የብሔራዊ መረጃ ሌሎች የታጠቁ ተጨማሪ የደህንነት አፋኝ ሐይሎች ህዝቡን አመሳስሎ ሊያስገባ መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆንበተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ የደህንነት ከፍተኛ አመራሮች አስተዳደሮችና ቁልፍ የስለላ ግለሰቦች ጎንደርን ለቀዉ እንዲወጡ ትእዛዝ ሲያስተላልፍ ህዝባቸዉ ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ለክክሉ የመከላከልና ዘመቻ ስምሪት ክፍል ትእዛዝ ቢተላለፍም የመከላከያ የጦር አባላትና፣ የአካባቢ ሚሊሻዎች እንዲሁም የክልሉ የፖሊስ አባላት አንዳች ጥይት እንደማይተኩሱና ህዝቡ ላይ ለሚወሰድ ማንኛዉንም አይነት እርምጃ የመከላከል ግዴታቸዉን እንደሚወጡ ለመረጃ ድርጅቱ በድፍረት ገልጸዋል።
በተያያዘ ሁኔታ አጋጣሚዉ የሰመረላቸዉ የዉስጥ አርበኞች በተጠናከረ መልኩ ህዝብን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የነበሩ አፋኝ ግለሰቦችን እያሳደዱ በማደን ላይ መሆናቸዉን የአርበኞቹ ምንጭ ጠቅሰዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
( ጉድሽ ወያኔ )
,
Aseged Tamene photo

Thursday 7 July 2016

ሁለት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ የተደረገው ሙከራ የህዝብ ቁጣ ቀስቅሷል

ባለፈው ሳምንት በአዲስ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀጣና 01 መንደር 06 በተለምዶ አጠራር ቀርሳና ኮንቶማ በሚባለው አካባቢ የሚገኙ ሁለት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ህዝቡ እየተቃወመ ነው።
ባለፈው ሳምንት ኡራኤል ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ሙከራ ሲደረግ ህዝቡ ባስነሳው ተቃውሞ ቤተክርስቲያኑ እስካሁን ሳይፈርስ ቆይቷል። ከሶስት ቀናት በሁዋላ ደግሞ የቤተክርስቲያኑ ቄስ በፌደራል ፖሊስ ተገድለዋል። አፍራሽ ግብረሃይሎች የጸበል ቦታውን ካፈረሱ በሁዋላ ፣ ሙሉውን ቤተከርስቲያን ለማፍረስ ህዝቡ ጽላት እንዲያወጣ ጠይቀዋል። ይሁን እንጅ ጽላቱን የሚያወጡ ቄሶችን ገድላችሁዋቸዋል በማለት ህዝቡ መልስ የሰጠ ሲሆን፣ ቤተክርስቲያኑም እስካሁን ከመፍረስ ድኗል። በተመሳሳይ ሁኔታም ኪዳነምረት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ዛሬ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ካህናቱ ግን ጽላት አናነሳም እያሉ ናቸው።
ህዝቡም ተቃውሞውን በመግልጽ ላይ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ እናት ድርጊቱ የእግዚአብሄር ቁጣ ነው ይላሉ።
መስተዳድሩ በወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ከ30 ሺ በላይ ዜጎች ያለመጠለያ ቀርተዋል። ከ300 በላይ ወጣቶችም ተይዘው ታስረዋል። የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ታሪክ ፍቅሬን ጨምሮ ሁለት ፖሊሶችም ተገድለዋል።

የህወሃት ብሔራዊ መረጃ በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ክትትል በተመለከተ የጥቂት ወራቶችን ሪፖርት ለሚመለከተዉ

የህወሃት ብሔራዊ መረጃ በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ክትትል በተመለከተ የጥቂት ወራቶችን ሪፖርት ለሚመለከተዉ አካል አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት የብሔራዊ መረጃዉን መድብለ ሪፖርት አጠርና ጠቅለል ባለ መልኩ ለሚመለከታችሁ ሁሉ ለማድረስ እንሞክራለን…
ኢሳትን 24 ሰአት ከማሳደድ ይልቅ ቃናን 24 ሰአት ማንጎድጎድ ስኬታማ ዉጤት እያመጣ ነዉ። ያለዉ የብሔራዊ መረጃዉ በተያያዘ መልኩ የተለያዩ የመሐበራዊ የመገናኛ አዉታሮችን ማለትም እንደ ዘሐበሻ የመሳሰሉ አደገኛ የተባሉትን ድህረ ገጾች ለማዳከም እና ለማጥፋት ተጨማሪ የበጀት እቅዶችን ዘርግቷል።
የብሔራዊ መረጃ ወንበድዉ ክፍል የኢትዮጵያ ህዝብ በብዛት ትኩረቱን ወደ ቃና ቴሌቪዥን እያዘነበለ እንደሚገኝና ኢሳትን እና ተዛማጅ የመረጃ አዉታሮችን የማዳመጡ እና የመከታተሉ ሁናቴ እንዲባረድና እና እንድጠፋ የተደረገ ሲሆን ይህ እንቅስቃሴ ስኬታማ ዉጤት እያመጣ ነዉ ይላል::
ይህ ብሐራዊ መረጃ ቃናን የመሰለ አደገኛ ህዝባዊ ጠላት በሐገራችን ላይ ተክሏል። ከመረጃ ክፍሉ አስገራሚዉ ተዉኔተ ሪርት ዉስጥ ቃና በሐገራችን ላይ ሊያስከትል የሚችለዉ አሉታዊ ተጽእኖ በማላገጥ መልኩ ዳሶታል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆንበ ለምሳሌ የሐሰት ቋት ስርጭት ክፍሉ ኢቢሲ ላይ ሊደርስ የሚችለዉ የዉድቀት አደጋ ሲሆን ይህዉም የማስታወቂያ እና የፕሮፓጋንዳ በተለይም ህወሃታዊ ድሰቶች ኪሳራ ላይ እንደሚወድቁ ሲብራራ አዉራ የማስታወቂያ ድርጅቶችም ፊታቸዉን ወደ ቃና እያዞሩ መሆኑ እንዲሁም የልማታዊ አርቲሶችን ቅሬታ በተመለከተ ጥቂት ተብሏል።
ነገር ግን የብሔራዊ መረጃዉ ኢቢሲን በተጭማሪ በጀት እና በድጎማ ማቆየትን እንደ መፍትሄ ሲያቀርበዉ ልማታዊ አርቲስቶቹን በተመለከተ ከቃና ጋር በመተባበር የትርጉም ድምጽ አገልሎት ላይ እንዲሳተፉ በሚል መልኩ ቀልዶባቸዉ ያልፋል የዚህ የብሔራዊ መረጃዉ እቅድ እንደሚያመልክተዉ ከሆነ በቅርቡ ከልማታዊ አር..ቲስቶቹ መካከል የሰራዊት ፍቅሬን እና የሙሏለምን ድምጽ በቃና ተከታታይ ድራማ ላይ እንደምናደምጠዉ ተስፋ አለን። የለቅሶ ዉጤት ነዉ!!!
ብሐራዊ መረጃዉ ተንኮለኛነቱን በማጉላት ረገድ ኢሳትንና መሰሎቹን በከፍተኛ ሁኔታ ለማዳከምና አዉራ ተወካዮችን በተለያየ መንገድ በማጥቃትና እና ከጨዋታዉ ለማውጣት . . . .ስም በማጥፋት፣ ቤተሰቦቻቸዉን በማነጋገርና በማሰር፣ እንዲሁም በድርድር፣ በማባበል፣ በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ኢኮኖሚያዉ ተጽኖ በመጣል የሚከወኑ የግፍ አፈጻጸሞች በዉስጡ ይገኙበታል።
የአፋኙ መደብ.. ብሔራዊ መረጃ በብዙ ሐገራት ተወዳጅ ያልሆነዉንና የስንፍና ቫይረስ ስርጭቱን ” የቃና ቴሌቭዥን “በኦሮምኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለህዝብ እንዲተላለፍ በማድረግ ኢሳት ላይ እየተተገበረ የሚገኘዉን የሚዲያ አፈና ዘዴ የነጃዋር መሐመድ የድካም ዉጤት በሆነዉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ላይ ለመፈጸም በጥብቅ እየሰራ ለመሆኑ ሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
ዉድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ ይህ የወንጀለኛዉ የብሔራዊ መረጃ መዋቅር ከኢስት እስከ ፌስ ቡክ ድረስ የተዘረጋ የመጨረሻ መፍጨርጨር መሆኑን እንድትገነዘቡ እያሳሰብን አቀጣዩ በፌስ ቡክ ላይ የሚያካሐዱትን ተራ የአፈና እንቅስቃሴ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ድል ለኢቶጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )