Wednesday 3 May 2017

በኮሎኔል ደመቀ ላይ መስክሮችን ለማሰማት ለግንቦት 28ና 29 ቀን 2009 ዓ.ም ተቀጠረ



በኮሎኔል ደመቀ ላይ መስክሮችን ለማሰማት ለግንቦት 28ና 29 ቀን 2009 ዓ.ም ተቀጠረ
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ የኔነህ ስሜ መታየቱ ታውቋል፡፡ ጉዳዩን የያዙት የክልሉ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ያየህ ስሜ ኮሎኔል ደመቀን በማረሚያ ቤቱ ውስጥ እየደረሰባቸው ያለውን በደል መቆም አለመቆሙን ጠይቀዋቸዋል፡፡ በእግራቸው ላይ የገባውን ሰንሰለት መነሳት አለመነሳቱን ጠይቀው ማረሚያ ቤቱ ሰብአዊ ክብሩን በጠበቀ ሁኔታ እንዲይዙት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
በግንቦት ወር ይቀርባሉ የተባሉት አብዛኛዎቹ ምስክሮች የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከኹመራና ወልቃይት የሚመጡ ሰፋሪዎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምስክሮቹ ቃላቸውን የሚሰጡት በሁለት ቀን እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ቁጥራቸውም 27 ናቸው ተብሏል፡፡ በኮሎኔል ደቀመ ላይ የተፈበረከው ክስ 165 ገጽ ሲሆን በእነ አቶ አታላይ ዛፌ ላይ ደግሞ 152 ገጽ ክስ እንደተሰጣቸው የሚታወስ ነው፡፡
በሌላ በኩል በወልቃይት የወረዳው ከፍተኛ ባለሥልጣን እና ባንዳ አቶ አቡሃይ ማሜ አዲግባ ላይ ገበሬዎችን ለማነጋገር የሄደ ቢሆንም ሕዝቡ ‹‹እኛ ዐማራ ነን ከዚህ በኋላ እንዳትመጣብን›› ብለው አባረውታል፡፡

No comments:

Post a Comment