Wednesday 28 October 2015

The Zone 9 Bloggers are Free: but Ethiopia Still Thinks Digital Security is Terrorism

The last of the Zone 9 Bloggers are finally free from jail, after nearly 18 months of detention for simply speaking out online. All the bloggers were acquitted of terrorism charges by the Ethiopian courts; one blogger, Befeqadu Hailu was found guilty of a single charge of “inciting violence” as a result of a confession made during his detention. He was released on bail last Wednesday. Given the time he has already served, he is unlikely to return to jail.
The victory of the bloggers over these baseless accusations of terrorism is a relief to everyone concerned: their friends, family, and their extended network of supporters around the world. However, it will not undo the months each of them unjustly spent in jail, in often horrendous conditions, isolated from their family and friends.
While Zone 9 bloggers are free, the Ethiopian government’s continues to threaten and incarcerate journalists and online speakers. According the Committee to Protect Journalists, 57 media professionals have fled Ethiopia in the last five years. All of Ethiopia’s commercial free press has been shuttered. Online, exiled media, and local citizen journalists have taken up some of its responsibilities but at great personal risk. Exiles are harassed and spied on, as our ongoing case Kidane v. Ethiopia demonstrates. Domestic writers continue to be accused of terrorism and thrown in jail for their work, including the journalist Eskinder Nega who on Friday spent his 15000th day in prison, four years into an 18 year jail sentence.
Diplomatic pressure from Ethiopia’s allies, including the United States, played its part in the Zone 9 case. But these campaigns are reactive, and can only help speakers who are well-known outside the country. What broader commitment could Ethiopia’s allies and business partners advocate for in Ethiopia, that could concretely make a difference to free expression in that country?
In the Zone 9 case, the heart of the prosecution revolved around Ethiopia’sAnti-Terrorism Proclamation of 2009. This law presents the harshest of penalties (each blogger faced up to ten years imprisonment) for the vaguest of offenses.
Ethiopia’s allies could certainly pressure the Desalegn regime to roll back the law. Unfortunately, the political cove—indeed the very mode—for the Anti-Terrorism Declaration comes from the domestic policies of those same countries. Teddy Workneh, a fellow at the University of Oregon, observes that Ethiopa’s anti-terrorism laws, which include broad definitions of terrorist support and weak protections against pervasive surveillance, borrow their structure from other post-911 laws in Europe and the Americas. That means that without legal reform of their own anti-terrorism legislation at home, countries like the United States can only weakly urge Ethiopia to “to refrain from using its Anti-Terrorism Proclamation as a mechanism to curb the free exchange of ideas,” rather than reject it outright.
There is, however, one step that every country critical of Ethiopia’s treatment of Internet users and journalists could take. Prosecutors in the Zone 9 case used the bloggers’ possession of digital security manuals, including guides to using encryption to protect communications, as evidence that they were involved in terrorist activities. International government organizations likethe United Nations, the OSCE, as well as the U.S. State department have all stated that encryption and secure communications are vital to free expression, or offered or funded digital security trainings to journalists.
Foreign governments that support these initiatives need to make it clear to allies like Ethiopia that the use of encryption and efforts to improve the security of one’s communications are not indicators of terrorist intent, but part and parcel of the modern journalist’s (or blogger’s) toolkit.
They could begin now by raising this matter in another case now passing through the Ethiopian courts: that of Zelalem Workagegne, Yonatan Wolde, Abraham Solomon, and Bahiru Degu. According to their colleagues, these Ethiopians are being detained on terrorism charges primarily because of an invitation they received to take part in a digital security training session outside of Ethiopia.
Ethiopian prosecutors are trying to turn the responsible practices of any journalist, blogger or concerned Internet user into evidence of terrorism. The international community needs to step forward and make clear that this case, and others like it, are as unacceptable as any other attack on the Ethiopian media. The Zone 9 Bloggers are free, but no more Ethiopians should face the ridiculous accusations simply for caring to protect their own online communications.

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡


ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡:
እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡ በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

Tuesday 20 October 2015

የጨቋኘ ስርአት እድሜ በጣት መቆጠር የሚጀምረው ህዝብ ስርአቱን መፍራት ሲያቆም ነው !! የፈራ ይመለስ ጎንደር

በጎንደር ከተማ  የመስቀል በአልን  አስታኮ  የታየው ድንገተኛ ህዝባዊ ቁጣ የወያኔ ስርአትን ሲያስደነግጥ ለለውጥ ናፋቂዎች ታላቅ ብርታት ሆኗል።
”የፈራ  ይመለስ” የሚል ጽሁፍ የተጻፈባቸው  ቀይ ካኒቴራዎች  የለበሱ 500 የሚደርሱ የጎንደር ወጣቶች የመስቀል በአል ደመራ  የሚበራበትን አካባቢ መነሻ በማድረግ በጋራ ሲዘምሩ ታይተዋል ፣ ይህም ሁኔታ  በስርአቱ አምስት ለ አንድ ተጠፍንጎል የተባለው ህዝብ መካከል 500 የሚደርስ ካናቴራ ታትሞ ለህዝብ እሲኪደርስ ድረስ ከካድሬዎች ጆሮ አለመድረሱ እርግጥም ህዝብ ያልተቀበለው ስርአት ምንም አፋኝ ቢሆን የህዝብን ፈላጎት ፍጹም መገደብ እንደማይችል ማረጋገጫ የለም ለሚሉ ስዎች  እነሆ  ምስክር ብለናል ።
ትልቁ ጉዳይ ግን የአምስት ለአንድን ቀመር በዚህ ሁኔታ  ላይ ብንስራው  በ500 ሰው መሃል 100 ካድሬ ይኖራል ማለት ነው እነዚህ መቶ ካድሬዎች ይህን እቅድ ሳይደርሱበት ቀርተው ይሆናል የሚል መከራከሪያ  ነጥብ ሊኖር ቢችልም  ካድሬ ተብለው ደሞዝ እየበሉ የተገላቢጦሽ የወያኔን ስርአት ለማፈራረስ የሚተጉ የውስጥ አርበኞች አሉ የሚለው ሃሳብ እጅግ አሳምኖኛል ።
የፈራ  ይመለስ የሚለው መፈክር የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኘ ፅሁፍ እርእስ ስትሆን ከስርአቱ ጋርም ደም ያቃባችው መሆንዋን የሚረሳት ያለ አይመስለኝም ፣ ቁስሉ የተነካው ወያኔም  ቂሙን  ለመመለስ የጎንደርን ህዝብ በገፍ ለስቃይ እየዳረገ መሆኑን የዜና  ማሰራጫዎች በሰፊው ዘግበውታል
ወያኔዎች አንድ ግልጽ ያልሆነላችው ነገር ቢኖር   የመለስ ራእይ በዱላ  የሚስርጽ ቢሆን ኖሮ አማኙ በዝቶ ፌደራል  ፖሊስ  ድሮ ገና  ስራ በፈታ  ነበር ምክንያትም በመንገድ ያገኙትን ስው ሁሉ ልቀቅ ፣ ተበተን  እይሉ ያልቀለጠሙት ስው  አለ ብዬ አላምንም እና ።  ቅልጠማውም ጥብጠባውም ያልበገረው ህዝብ ሆ  ሲል ላየው ወደ ትግል ሜዳ እየሄዱ ያስመስላቸዋል ፣ እርግጥ ነው አንድነቱ እና ድፍረቱ  ቢበረታታም መጪውን አገር አቀፍ ትግል ውጤታማ ለማድረግ  ከሚያምነው የትግል  አጋሩ ጋር ተደራጅቶ ለቀጣዩ ወሳኝ ትግል ራሱን በመንፈስ በማዘጋጀት ለሚተላለፉ ህዝባዊ ተልእኮዎችን በተጠንቀቅ የመጠበቅ ስራ መተኮር ያለበት ወቅታዊ ተግባር መሆኑን ማስታውስ ያሻል እላለሁ ።
ድል ለኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ

የህዝብ አደራ የበላው ሞላ አስገዶም በጠና ታሞ ጦርሃይሎች ሆስፒታል ግብቶዋል

የህዝብ አደራ የበላው ሞላ  አስገዶም በጠና ታሞ  ጦርሃይሎች ሆስፒታል  ግብቶዋል
ህዝብን አደራ በልቶ አገር አድን ሃይሉን ከድቶ ወደ ወያኔ ካምፕ የገባው ሞላ አስገዶም በስነልቦናዊ እና አካላዊ ህመም መስቃየት ላይ በመሆኑ ጦርሀይሎች ሆስፒታል ገብቶ በከፍተኛ ህክምና እርዳታ ላይ እንደሚገኘ አግ7 ዜና አስታውቆዋል።
ለእኩይ አላማው አሳስቶ በጠላት እጅ ያስገባችው ታጋዮች እየተስጣችው ባለው የምርኮኞች ስልጠና ተፈላጊውን ውጤት ለማምጣት ካለመቻሉም ባሻገር ለስርአቱ መቆየት ስጋት ይሆናሉ በሚል ከህዝብ ተገለው እንዲቆዩ አስልጣኞች መናገራችውን ያልተረጋገጡ ምንጮች ጠቁመዋል።ሞላ
  • facebook
  • twitter
  • rss
  • print
  • bookmark
  • email

“ድል ለአርበኞች ግንቦት 7!” “ሞት ለወያኔ!” የሚሉ ፅሁፎች በኢትዮጵያ ከተሞች እየተሰራጩ ነው

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ
“ድል ለአርበኞች ግንቦት 7!” “ሞት ለወያኔ!” የሚሉ እና ሌሎች ፅሁፎች በአርባ ምንጭ ከተማ በዋና ዋና ቦታዎች ላይ በብዛት ተለጥፈው ታዩ፡፡
Patriotic Ginbot7 flyers distributed in Ethiopian cities
ጠንከር ያለ የፀረ-ህወሓት ህዝባዊ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ የአርባ ምንጭ ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ጀግኖች የአርባ ምንጭ ወጣቶች በከተማዋ ውስጥ ተደራጅተው ከፍተኛና ያልተቋረጠ የነፃነት ተጋድሎ በማድረግ አንድነትንና ዴሞክራሲን ለማምጣት ደጋግመው የህይወት ዋጋ ሲከፍሉ ከመቆየታቸውም ባሻገር ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለየ ሁኔታ በረሃ እየወረዱ የትጥቅ ትግሉን መቀላቀላቸውን አሁንም በአስደማሚ ሁኔታ ቀጥለውበታል፡፡ ከአንድ ሰፈር ብቻ ከ15 በላይ ወጣቶች አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለው በከፍተኛ እልህ፣ ሞራል እና ወኔ በትግል ላይ ይገኛሉ፡፡
በበረሃ በእሳት በከተማ በእምቢተኝነት እየተፋለሙ ህወሓትን አላስቆም አላስቀምጥ ያሉት እነዚህ ጀግና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የአርባ ምንጭ ወጣቶች ከትናትና በፊት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም “ድል ለአርበኞች ግንቦት 7!” “ሞት ለወያኔ!” የሚሉ መፈክሮች በሰፈሩባቸው ሰፋፊ ወረቀቶች እና የግድግዳ ላይ ፅሁፎች አርባ ምንጭን ከፍነዋታል፡፡
ድል ፋና ቀበሌ፣ መናሃሪያ፣ ስታድየም፣ ወደ ማረሚያ ቤት የሚወስደው ጎዳና፣ የከተማዋ መግቢያና መውጫ ድልድዮች… መፈክሮች ከተለጠፉባቸው ቦታዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ይህ የአርባ ምንጭ ህዝብ የትግል መንፈስ ከፍታ ያስደነገጣቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ደህንነቶች እንደለመዱት ያገኙትን ወጣት ሁሉ እያፈሱ ወደ ወህኒ ማጋዛቸውን ተያይዘውት ይገኛሉ፡፡
የህወሓት ደህንነቶች ከወጣቶቹ አፈሳ ጎን ለጎን በስብሰባ ከመጠመዳቸው በተጨማሪ ወደ ገጠርም እየወረዱ “የሽብር ወረቀት ተበትኗል በጃችሁ ቢገባ እንዳታነቡት…” በማለት ለገበሬው ማህበረሰብም ማስጠንቀቂያ አዘል ሰበካ እያደረጉ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት የጀግኖቹ መዲና አርባ ምንጭ ከተማ እስከ አፍንጫቸው በታጠቁ የፌደራል ፖሊስ እና የልዩ ኃይል ጦር ዙሪያዋን ታጥራ ትገኛለች፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማም የተቃውሞ ወረቀቶች በሰፊው እንደተበተኑ ታውቋል፡፡

የቀድሞ ዴምሕት አባላት በወያኔ ፎቶገጭ ቤት (ነፃነት ዘለቀ)

ነፃነት ዘለቀ
እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ እንኳን ለአዲሱ ዓመት የ2008 ዓ.ም ሁለተኛ ወር “ለጥቅምት አንድ አጥንት” በሰላም አደረሳቹ፡፡ ጥቅምት ብርዳምና ንፋሳም ነው፡፡ ዘንድሮም እንደዛው ነው፡፡ የአዲስ አበባ የሰሞኑ ብርድ ሚስት ያሳቅፋል፡፡ ግን ስንገናኝ ሰላምታ የማንለዋወጠው ለምንድነው? ብዙ መጣጥጥፍ ጸሐፊዎች ይህን ወግ ልማድ ረስተው በቀጥታ ሊያስተላልፉት ወደሚፈልገጉት ቁም ነገር ይገባሉ – ያበሳጩኛል፡፡ “እንዴት ሰነበታችሁ” ማለት ማንን ገደለ? ኧረ ሳልረሳው – በመግቢያየ “አደረሳቹ” የሚል ቃል ሆን ብዬ ጽፌያለሁ፡፡ አማርኛ ቋንቋ በጣም ቅጥ አምባሩ እየጠፋ መምጣቱን ለመጠቆም ፈልጌ ነው እንዲያ ያልኩት፡፡ ትልልቅ የመሥሪያ ቤት ደብዳቤዎችን ብታዩ – አማርኛ አፍቃሪው ሕወሓት እንዳይቆጣኝ እንጂ – አማርኛው እንዴት እንደተመሰቃቀለ ልገልጽላችሁ አልችልም፤ በስማም! ውጥንቅጡ ወጥቶላቹሃል – እምልክ ገባክ? እንዲክም ስልክ በአንድ ወይ በሁለት አካባቢውች ብቻ እንዳይመስልክ – በሁሉም ቦቶችና ሥፍሮች ነው አማርንኛ እየተቀጠቀጠ ያለልክ፡፡ ምን እንደነካን አይታወቅም – ደግሞም “ዋናው መግባባት ነው” የሚል ፈሊጥ ተስፋፍቶልካል – ደካማ ጎንንና ስንፍናን መሸፈኛ ፈሊጥ ነው፡፡ “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ …” ‹ጨው ነጋዴ መልሶ ገዛው› እንዲሉ ነው ነጎሩ፡፡ ምን ይሻላል? “ እዚህም እሳት…እዚያም እሳት … እሳት.. እሳት” አለ ያ ታሪካዊ የኪነ ጥበብ ሰው ቴዲ አፍሮ በ17 መርፌ ዘፈኑ (“ጃን ያስተሰርያል” ለማለት ፈልጌ ርዕሱ ለጊዜው ተሰውጦብኝ ነው)፡፡Mola Asgedom's defection
ዋናው ሥራ አሥኪያጅ ወይም ሚኒስትር “…አስታውቃለሁ” መባል የሚገባውን “ …አስታውቃለው፡፡” የሚል ማሣረጊያ ቃል ያለው ደብዳቤ ላይ ፊርማውን አስቀምጦ በተላላኪው ሲሰድ ታያላችሁ – ዘመነ ድንቁርና ነው የገጠመን፤ ዘመነ ግዴለሽነትም ጭምር፡፡ እንዲያውም ይህ ዓይነቱ ስህተትማ ቀላልና ሊታገሱት የሚቻል ስህተት ነው፡፡ ይህን መሰል ከየቢሮው የሚወጣ ደብዳቤና በየቦታው የተለጠፉና የተሰቀሉ የማስታወቂያ ጽሑፎችን ብናይ አማርኛና እንግሊዝኛ በእግራቸው እየሄዱ እንደሆነ ማረጋገጥ እንችላለን፤ የጉራማይሌው ድረታ – የሆሄያት አጻጻፍ ችግር (የእስፔሊንግ ስህተት) … ግዘፍ ነስቶ “የቋንቋ መምህር ያለህ!” እያለ ነው – የቋንቋ መምህራኑ ራሳቸው ለምሳሌ “How is yours childs?” ወይም “ከአርዕስቶቹ ጋር የማይሄዱ ከባባድ ቃላቶችን ካለመጠቀም ተቆጠቡ” የሚሉ በሰዋስው ስህተት የታጨቁ ዐረፍተ ነገሮችን ሲናገሩ ልትሰማ ትችላለሀ – ጊዜው ነው፤ ጊዜውም ስህተትንና ነውረኝነትን እንደመልካም ዕሤት የሚቀበልና ሰዎችን ሳይወዱ በግድ የሚያባልግ ነው፡፡ ዕውር ለዕውር እየተማራ ሀገር ገደል ገባች! ወይ ወያኔ፤ በምን ዓይነት የሥኬት ጉዞ እየተምበሸበሹ እንደሆነ በጣም ጥቂቶች ብቻ ነን የምናውቀው፤ ዶግሞ’ኮ ይህ አደገኛ ሁኔታ የሚያሳስበውም ሆነ የሚያስጨንቀው አካል የለም፡፡ ተዓምር ነው፡፡ እንዲያው ለመግቢያ ያህል እንዲህ አልኩ እንጂ አነሳሴ ሌላ መሆኑን ርዕሴ በግልጽ ይናገራል፡፡ በዚህ በጠቀስኩት የቋንቋ አጠቃቀም ስህተት ልጻፍ ብልማ ወረቀት አይበቃኝም፤ የነገ ሰው ይበለኝ ግን፡፡ እንደሞትን ካልቀረን መገናኘታችን “ግድ ይላል”፡፡ ወይ አማርኛ! ኤርምያስ ለገሠ “ባለቤት አልባ ከተማ” ብሎ መጽሐፍ መጻፉን አትርሱ፡፡ “ባለቤት የሌለው እየጠፋ ያለ ቋንቋ” በሚል ‹አርዕስት› – ማለትም ርዕስ – ደግሞ አንዱ ይጻፍ፡፡
ዛሬ የወያኔን ቴሌቪዥን ድንገት አየሁ፡፡ ቤተሰቦቼ የቲቪ ጣቢያ (ቻናል) ሲቀያይሩ ድንገት EBC 1 የሚባለው የወያኔ ቱሪናፋ መስመር ላይ ይደርሳሉ(የስም መለዋወጥ የተፈጥሮ ጠባይን የሚለውጥና ውሸታምነትን በሕዝብ ዘንድ የሚያስረሳ ይመስል በኩረጃ የሚስተካከለው የሌለው ጦጣው ወያኔ ቲቪውን EBC አለና ወደ BBC, CBC, CNN,… ለማጠጋጋት ሞከረ – ማፈሪያዎች! ለመሆኑ “ኮርፖሬሽን” ምን ማለት ነው? አንድ የወያኔ ካድሬ እንደፈለገው ለሚያሽከረክረው ጥሩምባ መሥሪያ ቤት ይህ ስም ይከብደዋል፤ ነገሩ “ሲወልዱ አይታ ..” እንደሚባለው ነው፡፡ አሃ፣ ለስምማ “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አይተ ማነው ብፃይ ኃይለማርያም ደሳለኝ” ይባልስ የለም? ቂቂቂቂ…. እኔን ጠ/ሚኒስትር ያድርገ..ኝ!) ዝኮነ ኮይኑ የወያኔን ቲቪ እንደማላይ የምታውቀው ባለቤቴ ፊቴን አየት አድርጋ ልትቀይረው ስትል ተይው አልኳት – አለወትሮየ ተይው በማለቴ እየገረማት ተወችው፡፡ ቀርቦ የነበረው ዝግጅት የሞላ አስገዶም ልጆች በወያኔ ጋዜጠኞች ቃለ መጠይቅ እየተደረገላቸው የሚያሳይ ዶኩመንተሪ የሚመስል ፊልም ነበረ፡፡ እንደምንም ጨክኜ ለመከታተልና ምን እንደሚሉ ለመስማት የትግስት ፈረሴን ቼ አልኩና ማዳመጤን ቀጠልኩ፡፡
“የቀድሞ የዴምሕት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የ… ግንባር መሪ” የሚል የማዕረግ ቅጥያ በምስላቸው ግርጌ የተለጠፈላቸው ፍጹማን ባላገሮች ናቸው የሚጠየቁት፤ ባላገር ስል ያልተማሩና ሥልጣኔ ያልዳሰሳቸው ደናቁርት ማይማን ለማለት ፈልጌ እንጂ በሌላ መልክ እንዳትተረጉሙብኝ አደራችሁን – ፀጉር ስንጠቃ አልወድም፡፡ አነጋገራቸው፣ (የተሰጣቸው ሊሆን ቢችልም) አለባበሳቸው፣ የሰውነት መላ አኳኋናቸው፣ የቋንቋና የሃሳብ ግንኙነታቸው፣ እንኳንስ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሊመስሉ የዕድር ቤት ዘበኛም ሊሆኑ የማይችሉ ፋርጤዎች ናቸው – (ውይ ጉዴ – “ፋርጤ” ለካንስ “ፋርጣ” ከሚል የቦታ ስም የወጣ የወገን ቅጽል ነው፡፡ ግን ግዴለም “ባላገር” ለማለትም በፈሊጣዊ አገባብ ስለምንጠቀምበት እንደዚያ ተረዱልኝ – በቦታ አመልካችነቱ ከሆነ ብዙ ፋርጤ ጓደኞች አሉኝና በቃሉ ፈሊጣዊ አገባብ ቅር እንደማይሰኙብኝ አምናለሁ፡፡) እናም እነዚህን የመሰሉ ሰዎች በርግጥም ነፃ ሊያወጡን በረሃ ወርደው ከሆነ ከበፊቱ ስህተት ነበር ብቻ ሣይሆን እነሱን ፊደል ለማስቆጠርና ቀለም ለማስለየት እንዲሁም መጠነኛ የፖለቲካ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ እኛ ነበርን እነሱ ወደሚኖሩባቸው አካባቢዎች መውረድ የነበረብን፡፡ ሀገርንና ሕዝብን ነፃ ማውጣት ለካንስ እንዲህ ቀላል ኖሯል እንዴ? ቼጉቬራና ሆቺሚን እንደነዚህኞቹ ማይም ባላገሮች ነበሩ ይሆን? እኔማ ሣቄን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ደግሞም ሁሉ ነገር ተወነባበደብኝና ግራ ገባኝ፡፡ ነፃ አውጪ መጀመሪያ ራሱ ነፃ የወጣ መሆን አለበት፡- ከተራው ዜጋ በበለጠ ወይም በተሻለ የነቃ፣ የተማረና የተመራመረ፣ ለማንኛውም ዓይነት ግልብና ህንፍሽፍሽ አስተሳሰብ በቀላሉ የማይንበረከክ፣ የጠንካራ አቋም ባለቤት፣ የጠንካራ ዲስፕሊን ጌታ … መሆን ይገባዋል እንጂ እንደነዚህ ዓይነት ልፋጭ ዜጋ ነፃ አውጪ ቢባል የነፃነትን ዋጋ ከዜሮ በታች ማውረድ ነው፤ እውነቴን ነው የምለው – ደግሞም አሁን እነዚህን የመሰሉ ማፈሪያዎች ስላየሁ አይደለም – ነፃ አውጪ እንደዚህ ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ፡፡ ስለነፃነት ምንነትና አስፈላጊነት ምን አውቀውና ምን ገብቷቸውስ ነው ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ “ነፃ ሊያወጡ” በረሃ የወረዱት? ሞላ ራሱን ባለፈው ሰሞን ሳየው የተሰማኝ ስሜትም ይሄው ነበር፤ ከኔ የማይሻል ሰው ምን መሆኔንና እንዴት እንደምኖር ሣይረዳ ነው ነፃ ሊያወጣኝ የሚነሣ? ይህማ ልክ እንደወያኔ የወታደር አመላመል ማለት ነው፡፡ ወያኔና ወታደር ምልመላው ዓለምን ጉድ የሚያሰኝ ነው – ቢታወቅለት፡፡ አንድ አንቀጽ ጣልቃ ላስገባና እመለስበታለሁ፡፡
ይቺ “የሻቢያን ሜካናይዝድ ጦር፣ እግረኛ ጦር፣ .ቲሪሪም ቲሪሪም ‹እየጠራረግን› ከስምንት ሞቶ በላይ ሠራዊት ይዘን ከኤርትራ ምድር ወጣን” የሚሏት የነአስገዶም ንግግር በጣም ትገርመኛለች፡፡ እንዴት ነገሩ – ያን ጠረጋና የሰገሌን ጦርነትና ገና ወደፊት እንደሚደረግ የሚጠበቀውን ›ስፔስወር› የሚያስንቅ ድንቅ ጦርነት አንዳቸው እንኳን በሞባይላቸው ቀርጸው ያላሳዩን ለምን ይሆን? እንደዚህ ዓይነት ታላቅ ወታደራዊ ‹ኦፐሬሽን› ሲታቀድና ሲፈጸም ኮብላዩ የቀድሞ የዴምሕት ሠራዊት ይህን ታላቅ ጀብድ ቀርፆ እንዴት ለታሪክ አያስቀምጥም ወይንስ ገና በወያኔ ስቱዲዮ እየተቀናበረ ይሆን? ከማንም ወገን ሆኜ ሣይሆን እንደ አንድ ነፃ ታዛቢ ይህን “እየጠራረግን ወጣን” የሚሉትን ቀልድ ስሰማ ከማሣቅ አልፎ በጣም ያስገርመኛል – በውነትም ጠራርገው ከሆነ ከካርን የተሠሩ ወታደሮች በየበረሃው አርቲፊሻል ጠበንጃና የካርቶን ተዋጊ ጀቶችን ይዘው ቀሞው ነበር ማት ነው – እነዚህ ጀለንፎዎች ናቸው አንድን የሠለጠነና የታጠቀ ጦር ጠራርገው የሚወጡት፤ መሪዎቹ እነዚህ ከሆኑ ተመሪዎቹ ምን ዓይት ይሆኑ? ለምን በአግባቡ አይቀለድም? የቀልድም እኮ ጡር አለው፡፡ ደግሞም “ጄኔራል” ሞላ አስገዶም እጁን እያወናጨፈ እንዴት እንደጠራረጓቸው በሰውነት እንቅስቃሴ ተደራቢ “ቋንቋ” ሲገልጽ አንድም የሻቢያ ጦር የቀራቸው አይመስልም፡፡ እነሞላ በጣም ጀግኖች ናቸው ማለት ነው፡፡ ግን ግን ማስረጃ ስላላቀረቡ የሚሉት ሁሉ ከወታደር ቁጥር አንስቶ እስከ ግዳይ መጣሉ ድረስ ውሸት እንደሆነ መረዳት አይቸግረኝም – በበኩለይ፡፡ የወታደር ቁጥርን ካነሳሁ ዘንዳ ደግሞ ይህ ከዴምሕት አፈነገጠ የተባለ ጦር ከ70 እስከ 900 መሆኑ የሒሣብ ችሎታየን በእጅጉ ተፈታትኖብኛል(ለነገሩ ሀገራችን በዚህ የስታትስቲክስ አኀዛዊ መረጃ ጉዳይ አትታማም፡፡ ፈገግ በሉ፡- መንጌ የተጋነነ ቁጥር ይወድ ነበር አሉ፡፡ እናላችሁ በዘመቻ ፕላን ቀጠና ጽ/ቤት – ስድስት ኪሎ አ.አ.ዩ. ዋና በር ፊት ለፊት የሚገኘው – በተካሄደ አንድ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ለእርሻ ምቹ የሆነ(arable land) የቦታ ስፋት በካሬ ኪሎ ሜትር ተመንዝሮ በግብርና ሚኒስትሩ ሲነገር ከተሰብሳቢዎቹ ብዙዎቹ በሣቅ ፈነዱ አሉ – ነገሩ የገባቸው፡፡ ለካንስ ሞኙ ሚኒስትር ጓድ መንጌን ማስደሰቱን እንጂ የተናገረው አኀዝ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት መብለጡን ልብ አላለውም ኖሯል! እኛ እንዲህ ነን እንግዲህ!) በውቀቱ ሥዩም በአንዲት ዚቀኛ ጭውውቱ “የቁጥር ችሎታየ እንኳን እስከዚህም ነው ግን በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሰዎች ብዛት ከ7 እስከ 700 ይሆናል፡፡” ብሎ ነበር፡፡ እንግዲህ ይታያችሁ የነሞላ አስገዶም ቁጥር እንደወያኔና እንደነሞላ ከ800 በላይ ማለትም 900 ገደማ መሆኑ ነው፡፡ በሌላ መረጃ ደግሞ ከ70 የማይበልጡ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ እውነቱ የትኛው ነው? እውነት ከማን ጋር ናት? ሌሎች እንዲህ ሰኞ ማክሰኞ የእንክሻ ጨዋታ የሚጫወቱባት ከሆነ ለምን እውነት ራሷ እውነቱን አትነግረንም? ሁለቱን ደምረን አማካዩን እንውሰድ ወይንስ ቀን እንጠብቅ? … ውሸት ከዚህች ምድር የምትጠፋበትን ወቅት በጉጉት ከሚጠብቁ የዓለም ምሥኪን ዜጎች መካከል አንዱ መሆኔን ብገልጽ ጉረኛ ትዕቢተኛ ትምክህተኛ … ምናምነኛ እባል ይሆን? ልባል፡፡ ምን ቸገረኝ፡፡ እናም ሀሰት በእውነት የምትሸነፍበትንና ሁሉም ለኅሊናው ተገዢ የሚሆንበትን ቀን በከፍተኛ ጉጉት እጠብቃለሁ፡፡
ወያኔ ወታደር የሚመለምልበት የተለዬ መሥፈርት አለው፡፡ “ካጠናቀርኩት መረጃ” ውስጥ ከቃል ፈተናው አንደኛውን ጥያቄ ልንገራችሁ፡- “ዕንቁላል የጓሮ አትክልት ነው፤ እውነት ወይንስ ሀሰት?” ለዚህ ጥያቄ “እውነት” ብሎ የሚመልስ ተመልምሎ የሚቀጠርና እንደነገሩ ሠልጥኖ ወያኔ ለፈለገው ግዳጅ የሚሠማራ ሲሆን “ሀሰት” ብሎ የሚመልስ ግን አንጎሉ ስለሚሠራ የወያኔን የውትድርና መሥፈርት አያሟላምና አይቀጠርም፡፡ በተረፈ የወያኔ ወታደር ከመጠነኛ የመግባቢያ ደረጃ ባለፈ አማርኛ ቋንቋ እንዲያውቅ አይጠበቅበትም – ብዘውን ጊዜም ከአማራው አካባቢ ወታደር አይቀጠርም ከደቡብና ከጋምቤላ ነው ይበልጡን የሚመለመለው፤ የትምህርት ደረጃም ምናልባት ከማንበብና መጻፍ ባለፈ አይፈቀድለትም፤ ከዜጎች ጋር ተግባብቶ መኖር ምሕረት የለሽ ቅጣት ያስቀጣዋል፤ በአንድ ቦታ ግፋ ቢል ከሦስት ወር በላይ እንዲቆይ አይደረግም (ከሕዝብ ጋር እንዳይግባባና የርህራሄ መንፈስ እንዳይኖረው)፣ ከወታደሮችም ጋር ሆነ ከሲቪሎች ጋር እንዲገናኝና ብሶቱንም ሆነ ሌላ ነገር እንዲያወራ አይፈቀድለትም – በቡድን ሆኖ መቆምና መቀመጥም ሆነ ማውራት በወያኔ የጦር ሠፈር ነውር ነው(የነሱው ምርጥ ሰው ማለትም ዘውጋዊ ቁርኝት ያለህ የውድቡ አባል ከሆንክ ይህ ህግ አይመለከትህም)፣ አንድ የወያኔ ወታደር ግደል ሲሉት እነማንንና ስንት ብሎ ካልሆነ በስተቀር ለምን ብሎ መጠየቅ አይችልም – ቢጠይቅ ከጭፍን እንስሳዊ ታዛዥነት ወደሰውነት ደረጃ እንደተለወጠ ተቆጥሮ መፈጠርን የሚያስረግም እርምጃ ይወሰድበታል ወይም ዕድል ከቀናው ይባረራል – ለዚህም ነው ፌዴራል ሲባል ተግባሩ ሁሉ በአረመኔነት የተሞላው – ደግሞም ተከታታይና ታዛቢ ስለሚመደብበት ቢራራ ራሱን ችግር ውስጥ ይከታልና ሳይወድ በግዱ ይጨክናል – ጥሎ ካልጠፋ በስተቀር ሕይወቱ እንደዚህ ባለ መርገምት ውስጥ የታጠረ ነውና ብዙም አንፍረድበት – ይህም ሥራ ሆኖ ሥራውን ቢለቅ ሌላ መኖሪያ የለውም፤ ድህነት ያጨክናል፤ ድህነት የለዬለት ጭራቅ ያደርጋል፤ የመኖር ጉጉት ከሰውነት ተራ ያወጣል፡፡ ስለዚህም በየከተማው የምናያቸው መለዮ ለባሾች ሰው ሣይሆኑ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀሱና ማኅበረሰቡን ወያኔ እንደሚፈልገው አንቀጥቅጠው ለመያዝ የተመደቡ ሥጋ-በል ዐውሬዎች ናቸው፡፡ ወታደር ስናይ የኛ ስለማይመስሉን እንሸሻቸዋለን፤ ፖሊስ እንደሚሻለን በእግረ መንገድ መጠቆሙ ግን አግባብ ነው፡፡ የወፓንና የፌዴራል ተብዬውን ወታደር ግን ተውት፤ እነሱን ስታስብ ጥሩ እንቅልፍ ላይዝህ ይችላል – ያቃዥሃል፡፡ አንተ ቀንቶህ ባትገረፍና ባትደበደብም ሌላው ወንድምና እህትህ ስለሚሰቃይ ቁስላቸው አንተንም ይጠዘጥዝሃል – ሰው ከሆንከ፡፡ ግን ስንታችን እንሆን ሰው? ይህም አጠያያቂ ነው፡፡
ፋርጤዎቹ የሞላ ልጆች አሳዘኑኝ፡፡ ደግሞም ወያኔ በተለመደ ቅጥፈቱ “የብሔር ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን” ተዋፅዖ ለማሟላት ከሚል ከንቱ ልፋት አንዱን ከደቡብ አንዱን ከሰሜን አንዱን ከምሥራቅ አንዱን ከምዕራብ እያደረገ ነው ቃለ መጠይቅ ያካሄደው፡፡ ሌላውና ለዚህ አጭር መጣጥፍ መጻፍ የወዲያው ምክንያት የሆነኝ እነዚህ የቀድሞ የዴምሕት “ከፍተኛ ባለሥልጣናት” (አላውቅም- ሊሆኑም ይችሉ ይሆናል፤ ማረጋገጫ እስካገኝ ግን ማላገጤም ይቀጥላል) ቃለ ምልልሱን ያካሄዱት ልክ እንደፎቶ ገጭ የመታወቂያ ፎቶ ማንሻ ወንበር አንድ ወንበር ላይና አንድ ግድግዳ አጠገብ ነው፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ ለባለቤቴ እያሳየሁ ሳቅንባቸው፡፡ ከ25 ዓመት የሥልጣን ዘመን በኋላም ፋራነቱን ሊቀርፍ ያልቻለ የመንግሥትን ሥልጣን የያዘ የወንበዴ ቡድን በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ማየት የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው እንኳን እንዴት አይነቃምና ይህን ቀላል ችግር ማስተካከል አልተቻለም? አምስት ይሁኑ ስድስት ተጠያቂዎች ሁሉም የተቀመጡበት ወንበር አንድ ነው፡፡ ቦታውም አንድ ነው፡፡ በራስጌያቸው መስኮት አለ፤ በግራ ጎናቸው በር አለ፤ በቀኛቸው መረብ የለበሰ በር ይሁን ጣሪያ አለ፡፡ እንዳልዋሽ ያህል ሰውዬው ሲቀመጥ ወዲያና ወዲህ ስለሚገፋውም ሊሆን ይችላል ወንበሩ ከመስኮቱ ወዲህ ወይም ወዲያ እየሆነ በጣም መጠነኛ ለውጥ በአንዳንዶቹ ተጠያቂዎች ላይ ይስተዋላል እንጂ አቀማመጣቸው የሁሉም አንድ ዓይነት ነው – የኛ የቀድሞ ነፃ አውጪዎች፣ የአሁን የወያኔ ባሮች፡፡ ወያኔ ማለት “አታምሪ ወይ አታፍሪ” የሚባል ዓይነት የክፍለ ዘመኑ ጉድ ነው – “ወላድ አይይህ” የሚባል ጉድ፡፡ ግን ግን ይህን ያህል የአገዛዝ ዘመን ለዚህ የወያኔ ግሪሣ የሰጠው ማን ይሆን? እኛ? ሰይጣን? ድግምትና መተት? ምዕራባውያን? የገዛ ኃጢኣታችን? እግዚአብሔር? ብልጣብልጥነታቸው? የአስተዳደር ዕውቀትና ጥበባቸው? ጭካኔያቸው? ጉልበታቸው? የኛ ሞልፋጣ ባሕርይ? ወይንስ ማን?
በአርምሞ አስቡት፡፡ በጥቂት ሽፍቶች አገር ሲታመስ ማየት፣ ብዙ ዜጋ በእግር አውጪኝ አገር ጥሎ እየተሰደደ ራሱንና ቤተሰቡን ብቻ ከሽፍቶቹ የእሳት ጨንገር ነፃ ለማውጣት ሲሯሯጥ መታዘብ የማያመልጡት የክፍለ ዘመናችን እርግማን ሆነ፡፡ ማን ለሐዝብ ያስብ? ማን ለሀገር ይቆርቆር? ማን ለትውልድና ለታሪክ ይጨነቅ? ይህን በስብሶ ሊወድቅ የደረሰ የወያኔ ቤተ መንግሥት ማን ይግፋው? መቼስ በራሱ አይወድቅ፡፡ ትንሽም ቢሆን ገፊ ኃይም ያስፈልጋል፡፡ ራስ ወዳድነት በነገሠበት ዘመን ያ ከየት ይምጣ? እኔም አንተም አንቺም … የምንጨነቀው ስለራሳችን ሆነ፡፡ ነገን ትተን ዛሬ ላይ ብቻ አተኮርን፡፡ የጋራ ህልምና ራዕይ አጣን፡፡ ምን ይዋጠን?
ታስታውሳላችሁ መቼም – አንዳርጋቸውን በቲቪ ሲያቀርቡ ከበስተጀርባው የነበረው “ሳውንድ ትራክ” የታይታኒክን ፊልም ያጀበው የሴሌንዲዎን ዘፈን ወይም የቦብ ማርሊ “stand up for your right” ሣይሆን የሚገረፍ ሰው የሚያሰማው የስቃይ ድምፅ ነበር፡፡ አቡበከርን አንድ “ ምሁር ፈላስፋ”ና “ግሩም አንባቢ” የወያኔ ካድሬ ከካሜራ ተደብቆ በግዳጅ ቃሉን ሲቀበል በዓለም የእሥረኞች ምርመራ ታሪክ (በቲቪ ለሕዝብ በሚቀርብ ማለቴ ነው) ምናልባት የመጀመሪያው ሊሆን በሚችል መልኩ እጆቹን በካቴና አሥረው ነበር – የግፍ ግፍ፤ ወያኔዎች ምንም ዓይነት ሥነ ምግባር (ethics) እንደሌላቸው በዚያች ልይት ኹነት ብቻ ለዓለም አስመስክረዋል፡፡ በቅርቡም የ“ዓለምን መሪ” በኢትዮጵያ ሲቀበሉ ያደረጉት መስተንግዶና መሪውን ለማየት ሲተራመሱ ያሳዩት የፋርጤ ድርጊት ሲታይ የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ አለማወቅ ብቻ ሣይሆን ሀገሪቱን ለማዋረድ ሆን ብለው ታጥቀው የተነሱ ይመስላሉ – እርግጥ ነው ከእረኞች ከዚህ የበለጠ መጠበቅ የዋህነት ነው፤ አብዛኞቹ ሞፈር ቀምበር ሰቅለው የመጡ ገበሬዎች ወይም ከፍየል ጥበቃ በቀጥታ ወደ መንግሥት ሥልጣን ያመሩ እረኞች ናቸው፤ በዚያ ላይ ነባር አሠራርን – ዓለም አቀፋዊም ቢሆን – የመጠየፍና ያለመቀበል ጠባያቸው የጎላ ነው፡፡ እንዲያው ለመሆኑ ግና እነዚህን የዮዲት ጉዲት ውላጆች ሊያጠፋ የሚችል በሀገራችን እንዴት አንድ ወንድ ይጥፋ? እነሱስ ምን ዓይነት “ዕድለኞች” ይሆኑ? ለነገሩ ከ1.2 ሚሊዮን ሕዝብ 11 ጀግና ልጆች ተገኝተው ትሪንዳድና ቶቤጎን አንድ ወቅት ለዓለም ዋንጫ ሲያበቁ ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል 11 ሰው ጠፍቶ ለአፍሪካ ዋንጫ እንኳን አለመብቃታችን … ግን ይህን ለምን እዚህ አመጣሁት በል? አስፖርትና ፖለቲካስ ምን አገናኛቸው … ስለዚህ ወሬ አለቀብኝ ማለት ነውና ሌላ ነገር ሳልዘባርቅ በጊዜ ልሰናበት ምዕመናን፡፡

Friday 9 October 2015

7.5 million going hungry as Ethiopia crisis worsens

Addis Ababa (AFP) – The number of hungry Ethiopians needing food aid has risen sharply due to poor rains and the El Nino weather phenomenon with around 7.5 million people now in need, aid officials said Friday.The number of hungry Ethiopians needing food aid has risen
That number has nearly doubled since August, when the United Nations said 4.5 million were in need — with the UN now warning that without action some “15 million people will require food assistance” next year, more than inside war-torn Syria.
“Without a robust response supported by the international community, there is a high probability of a significant food insecurity and nutrition disaster,” the UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs, OCHA, said in a report.
The UN children’s agency, Unicef, warns over 300,000 children are severely malnourished.
The Famine Early Warning Systems Network (FEWS NET), which makes detailed technical assessments of hunger, predicted a harvest “well below average” in its latest report.
“Unusual livestock deaths continue to be reported,” FEWS NET said. “With smaller herds, few sellable livestock, and almost no income other than charcoal and firewood sales, households are unable to afford adequate quantities of food.”
Ethiopia, Africa’s second most populous nation, borders the Horn of Africa nation of Somalia, where some 855,000 people face need “life-saving assistance”, according to the UN, warning that 2.3 million more people there are “highly vulnerable”.
El Nino comes with a warming in sea surface temperatures in the equatorial Pacific, and can cause unusually heavy rains in some parts of the world and drought elsewhere.
Hardest-hit areas are Ethiopia’s eastern Afar and southern Somali regions, while water supplies are also unusually low in central and eastern Oromo region.
Food insecurity is a sensitive issue in Ethiopia, hit by famine in 1984-85 after extreme drought.
Today, Ethiopia’s government would rather its reputation was its near-double-digit economic growth and huge infrastructure investment — making the country one of Africa’s top-performing economies and a magnet for foreign investment.
Still, nearly 20 million Ethiopians live below the $1.25 poverty line set by the World Bank, with the poorest some of the most vulnerable to weather challenges.
Ethiopia’s government has mobilised $33 million (30 million euros) in emergency aid, but the UN says it needs $237 million.
Minster for Information Redwan Hussein told reporters at a recent press conference that Ethiopia is doing what it can.
“The support from donor agencies has not yet arrived in time to let us cope with the increasing number of the needy population,” he said.

‹‹ለችግሮቻችን ምንጭ የሆነውን ስርዓት በቁጥርጠኝነት መታገል አለብን››ሰማያዊ ፓርቲ


Semayawi Party- Ethiopia's photo.
Semayawi Party- Ethiopia's photo.Semayawi Party- Ethiopia's photo.
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ መስከረም 27/2008 ዓ.ም በፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው ‹‹ረሃቡ የገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት ነው!›› በሚል በሰጠው መግለጫ ‹‹ገዥው ፓርቲ ችግር ቢከሰት እንኳ በአደጋ ጊዜ ለዜጎች የሚበቃ እርዳታ አቀርባለሁ ሲል የነበረ ቢሆንም ለወገኖቻችን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም፡፡›› ሲል ወቅሷል፡፡ ‹‹ለዜጎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዳይደርሱላቸው የተፈጠረው ረሃብ የራሱ የፖሊሲ ውድቀት መሆኑን የሚያውቀው ስርዓቱ የዜጎቻችን ስቃይና መከራ ሲሸፋፍን እንደቆየና ከአቅሙ በላይ ሲሆን ችግሩ እንደተከሰተ ቢገልፅም ለዜጎች ተገቢውን እርዳታ በሚያስገኝ መልኩ እርምጃ እየወሰደ አይደለም›› ብሏል መግለጫው፡፡ ለተከሰተው የረሃብ አደጋ ተገቢው ትኩረት መነፈጉም ገዥው ፓርቲ እመራዋለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ ቢስነቱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ፓርቲው በመግለጫው ‹‹ረሃቡ፣ ርዛቱ፣ ድህነቱ፣ ስደቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ የኑሮ ውድነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዜጎችን በብርቱ እየተፈታተኑ በሚገኝበት ወቅት ገዥው ፓርቲና በስሩ ያሉ ድርጅቶች ተመሰረትንበት የሚሉትን ጊዜ ለወራት በቅንጦት በማክበር በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ጉሮሮ ነጥቆ ድግስ ሲደግስና አሸሸ ገዳሜ ሲል በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፡፡›› ብሏል፡፡ ለተከሰተው ረሃብ ኢህአዴግ ለይስሙላ ቆሜለታለሁ የሚለውን አርሶ አደርና አርብቶ አደርን ህይወት ለማሻሻል የረባ ስራ እንዳልሰራ አረጋግጧል ያለው መግለጫው ግብርናው ኢኮኖሚውን ይመራል ቢልም እስካሁን ግን በየአመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የረሃብ ሰለባ እንደሆነ መቀጠሉን ገልፆአል፡፡ መሬት የመንግስት ነው በሚል ሽፋን አርሶ አደሩን ከቀየው እያፈናቀለ ለስርዓቱና ደጋፊዎችና ለባዕዳን መሬትን እየሸጠ አርሶ አደሩን ለረሃብ ተጋላጭ አድርጎታል ሲልም ለርሃቡ ምክንያት የኢህአዴግን የፖሊሱ ውድቀት እንደሆነ ገልፆአል፡፡
ገዥው ፓርቲ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀው ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ችግሩ ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያስረዳ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ በረሃብ ለተጠቁት ዜጎች መፍትሄ እንዲፈለግም ጠይቋል፡፡ ስርዓቱ ደካማና ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ የገለፀው ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያውያንና የዓለም ማህረሰብ ማህበረሰቡ ከተጎጅዎቹ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያውያን መከራ የመነጨው ከገዥው ፓርቲ የተሳሳተ ፖሊሲ፣ የአፈፃፀም ብቃት ችግርና ለኢትዮጵያውያንም ባለው ግድ የለሽነት በመሆኑ ለችግሮቻችን ምንጭ የሆነ ስርዓት በቁጥርጠኝነት መታገል አለብን›› ሲልም ለህዝብ ጥሪ አቅርቧል፡፡ፓርቲው ረሃቡ በተከሰተባቸው አካባቢዎች መረጃ በማሰባሰብና በማጣራት ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ገልፆል፡፡

‹‹ሞራልን ለመመለስ መፍትሄው፣ ነቅቶ ዕውቀትን መጨመርና እምቢ ማለት መቻል ነው›› ተማም አባቡልጉ /ጠበቃ/

‹‹የማታምንበትን ሀሳብ ደግፈህ መከራከር የሞራል ዝቅጠት ነው፡፡ አምባገነኖች ይሄንን ያስደርጋሉ፡፡ ሳታምን ያደራጁሃሉ! ሳታምን ሰልፍ ያስወጡሃል! ሳታምን እንድትናገር ያደርጉሃል! ሳታምንበት አንድን ነገር እንድትወድ እና እንድትጠላ ያደርጉሃል! ይሄ ሞራልን ይፈታተናል፡፡ ዕምነት የስሜት፣ የእውቀትና የሞራል ውህደት ነው፡፡ አምባገነኖች እያንዳንዱ ትልልቅ ነገሮቻችንን እየናዱብን ይገኛሉ፡፡ እውነተኛ የስሜት ጣዕም መለኪያዎቻችንንም ለጥቅማቸው ሲሉ በተለያዩ ዘዴዎች ይቀያይሩብናል፡፡ … ሞራልን ለመመለስ መፍትሄው፣ ነቅቶ ዕውቀትን መጨመርና እምቢ ማለት መቻል ነው፡፡ ያኔ የማታምንበትን ነገር አላንበትም ብለህ ፀንተህ መቆም ትጀምራህ፡፡ ››
Elias Gebru Godana's photo.

Tuesday 6 October 2015

"Låt Hanna stanna!"


Foto: Lina Rigney Thörnblom
Igår demonstrerade kampanjen Låt Hanna Stanna ochAsylrörelsen Stockholm utanför Riksdagen. Många av Hannas skolkamrater och lärare deltog. Hanna Tadesa går sista året på gymnasiet i Haninge och har bott i Sverige i fem år efter att ha flytt från Etiopien (Läs mer här). Budskapet på demonstrationen var tydligt: vi ger oss inte förrän Hanna Tadesa fått uppehållstillstånd, Sverige ska inte utvisa till Etiopien eller andra diktaturer.

– Hanna kom hit som tonåring, med drömmar. Hon fick en fosterfamilj, lärde sig ett nytt språk. Sverige gav Hanna framtidshopp, drömmen om att bli kock. När Hanna blev vuxen enligt lag – då drog Sverige undan mattan. Med åtta månader kvar av utbildningen släcker Sverige hennes framtidsa läraren Tuija Kirvesmies från kampanjen Låt Hanna Stanna.
Tuija Kirvesmies (talar) och Hanna Tadesa.
Foto: Lina Rigney Thörnblom
Khashayar Shahrezaei talade för Iranska flyktingars riksförbund:
– Vi får hela tiden höra prognoser om hur många asylsökande som kan tänkas komma till Sverige varje år. Men vad vi knappt får veta är hur det går för majoriteteten som får avslag och lever här som papperslösa. Det har blivit svårare för papperslösa att få uppehållstillstånd när de söker asyl för andra gången. Även om de levt i Sverige i många år och rotat sig. Människor som har gått igenom många hemskheter, som försöker glömma det liv man haft bakom sig och titta framåt.

Etiopiska flyktingföreningen redogjorde för hur Etiopien kriminaliserar och kränker sitt eget folk, exempelvis genom sin terrorlagstiftning vilken innebär att alla som umgås, träffar eller fångas på bild med någon som är regimkritisk kan dömas som terrorist. Detta innbär att familjemedlemmar till regimkritiker automatiskt blir en måltavla för regimen, som Hanna Tadesa blev när hon fängslades, torterades och våldtogs på grund av sin pappas politiska arbete.

Lina Rigney Thörnblom (RS)
Foto: Ada Salomón
– Sverige är bundet av internationella konventioner som förbjuder utvisning av människor som riskerar tortyr. Ändå har Sverige fällts fler än 20 gånger av FN:s kommitté mot tortyr för att ha gjort just det. Utvisningarna är en del av ett system, sa Rättvisepartiet Socialisternas kommunfullmäktigeledamot Lina Rigney Thörnblom och förklarade att medan etablissemanget säger att det inte finns pengar, jobb eller bostäder så har staten öst pengar över bankerna.

Lina talade också om hur uppehållstillstånd kunde vinnas åt haningeeleven Laziz Sharifov, genom ockupationer av Migrationsverket och genom engagemanget bland Laziz klasskamrater och lärare.

På demonstrationen skrev många upp sig att bli aktiva i den fortsatta kampanjen, bland annat i Studenter mot Rasism som organiserar elever och studenter på en rad skolor i Stockholm och i landet. Kampen för asyl åt Hanna Tadesa och för att stoppa utvisningarna fortsätter!

- - - - -
Asylrörelsen Stockholm:
Asylrörelsen Stockholm är ett nätverk där Etiopiska flyktingföreningen, Studenter mot Rasism, Iranska flyktingars riksförbund och Rättvisepartiet Socialisterna bland annat ingår. Sedan starten 2011 har Asylrörelsen Stockholm stoppat deportationsförsök av nio politiska flyktingar på Arlanda tillsammans med passagerare och har drivit offentliga kampanjer som bidragit till uppehållstillstånd åt 19 flyktingar.

Protest krävde: Låt Hanna Stanna!


Hanna Tadesa till höger, vars kamp för rätten till asyl fortsätter. (foto: Lina Rigney Thönblom)
Hanna Tadesa till höger, vars kamp för rätten till asyl fortsätter.
Många av Hanna Tadesas vänner, skolkamrater och lärare samlades på måndagen utanför riksdagen för att demonstrera mot att hon hotas av utvisning till Etiopien. Även flera föreningar och organisationer kom för att visa sitt stöd.
Hanna Tadesa går det sista året på gymnasiet i Haninge och har bott i Sverige i fem år efter att ha flytt från Etiopien som sextonåring. Budskapet på demonstrationen var tydligt: vi ger oss inte förrän Hanna Tadesa har fått uppehållstillstånd – Sverige ska inte utvisa till Etiopien eller andra diktaturer.
– Hanna kom hit som tonåring, med drömmar. Hon fick en fosterfamilj, lärde sig ett nytt språk.Sverige gav Hanna framtidshopp, drömmen om att bli kock. När Hanna blev vuxen enligt lag – då drog Sverige undan mattan. Med åtta månader kvar av utbildningen släcker Sverige hennes framtid, sade läraren Tuija Kirvesmies från kampanjen Låt Hanna Stanna.
Khashayar Shahrezaei talade för Iranska flyktingars riksförbund:
– Vi får hela tiden höra prognoser om hur många asylsökande som kan tänkas komma till Sverige varje år. Men vad vi knappt får veta är hur det går för majoriteteten av dem som får avslag och lever här som papperslösa. Det har blivit svårare för papperslösa att få uppehållstillstånd när de söker asyl för andra gången, även om de har levt i Sverige i många år och rotat sig. Det är människor som har gått igenom många hemskheter och som försöker glömma det liv man haft bakom sig och titta framåt.
Etiopiska flyktingföreningen redogjorde för hur Etiopien kriminaliserar och kränker sitt eget folk, exempelvis genom sin terrorlagstiftning vilken innebär att alla som umgås, träffar eller fångas på bild med någon som är regimkritisk kan dömas som terrorist. Detta innbär att familjemedlemmar till regimkritiker automatiskt blir en måltavla för regimen, som Hanna Tadesa blev när hon fängslades, torterades och våldtogs på grund av sin pappas politiska arbete.

– Sverige är bundet av internationella konventioner som förbjuder utvisning av människor som riskerar tortyr. Ändå har Sverige fällts fler än 20 gånger av FN:s kommitté mot tortyr för att ha gjort just det, sade Rättvisepartiet Socialisternas kommunfullmäktigeledamot Lina Rigney Thörnblom och förklarade att medan etablissemanget säger att det inte finns pengar, jobb eller bostäder har staten öst pengar över bankerna.
Lina talade också om hur uppehållstillstånd kunde vinnas åt Haningeeleven Laziz Sharifov, genom ockupationer av Migrationsverket och genom engagemanget bland Laziz klasskamrater och lärare.
På demonstrationen skrev många upp sig att bli aktiva i den fortsatta kampanjen, bland annat i Studenter Mot Rasism som organiserar elever och studenter på en rad skolor i landet. Kampen för asyl åt Hanna Tadesa och för att stoppa utvisningarna fortsätter. ■

የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት “የተቃዋሚዎች ሬድዮ ታዳምጣላችሁ በሚል እየታሰሩ ነው


በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው የስብሰባው መሪዎችና ገምጋሚዎች ሆነው በመቅረብ ለበርካታ የሰራዊቱ አባላት እያባረሩና እያሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በተለይ በሰሜን እዝ እየተካሄደ ባለው የዓመቱ ግምገማ ላይ የሰራዊቱ አባላት ሓቀኛና ገምቢ ግምገማ ነው ብለው ስላላመኑበት ማንኛውም ሃሳብ ከመስጠት እንደተቆጠቡና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሆኑት የበላይ መኮነኖች “እዚህ የተሰበሰብነው ሰራዊቱ አንዣቦበት ካለው የመበታተን አደጋ ለማዳን ስለሆነ የተቃዋሚዎች ሬድዮ ለምን ትሰማላችሁ ብለው ላቀረቡት ሃሳብ በተሰብሳቢዎቹ ማንኛውም ሚድያ መከታተል የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብት ነው” ብለው የተቃወሙትን የናንተ አመለካከት ከተቃዋሚዎች ጎራ ነው በማለት እንድፋሰርዋቸው መረጃው ጨምሮ አስርድቷል።..

የተቸካዮች ምክር ቤት /በበውቀቱ ስዩም/

ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግ እንሞክራለን፡፡ ፊልም ዛሬ እንዲህ ጥንቡን ሊጥል ያኔ በጣም ብርቅ ነበር፡፡ ፊልም ሰሪዎች እንኳ እኛ ፊልም ለማየት የምንከፍለውን ያክል መስዋእትነት የሚከፍሉ ኣይመስለኝም፡፡ ያኔ ፊልም ማየት የጫማና የግስላ ሲጃራ ድብልቅ ሽታ የመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል ፡፡ እናም በጊዜው የሁለት ሰኣት ፊልም ኣይተን የሁለት ሳምንት ጉንፋን ተረክበን ለመውጣት እንገደድ ነበር፡፡
ኣሁን ሳስበው፤ ከፊልሙ በላይ የፈረንሳይ ልጆች በፊልሙ ላይ ተመስርተው የሚሰጡት ኣስተያየት ያዝናናኝ ነበር፡፡ ኣንድ ቀን በጣም እጅ እጅ የሚል ፊልም ስናይ “ፓርላማውን ቀይርልን ፓርላማውን ቀይርልን ”ብለው ቀወጡት፡፡ ኣሰልቺ ፊልሞች” ፓርላማ “ተብሎ እንደሚጠሩ ያወኩት ያኔ ነው፡፡ ባለቪድዮ ቤቱም ኣብላጫውን ድምጽ ኣይቶ ሌላ ፊልም እንዲቀየር ውሳኔ ኣስተለለፈ፡፡
የተወሰኑ የተቃዋሚ ድምጾች በሚሰሙበት ሰሞን እንዳሰልቺ ፊልም ይታይ የነበረው ፓርላማ ዛሬ ይሄ ኣይነቱ ኣጠራር እንኳ የሚበዛበት ይመስለኛል፡፡ እኔን የሚገርመኝ የተወካዮች ምክር-ቤት የሚለውን ስም እስካሁን ይዞ መቆየቱ ነው፡፡ የሚወከልም ሆነ የሚማከር በሌለበት ይሄን ስም መሸከም ኣይከብድም? እንዲያው ቤቱ ስሙ ከብዶት ኣለመፍረሱ ይገርማል፡፡
ያገራችን ፓርላማ ኋላቀር መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ግን ከመቶ ኣመት በፊት ከነበረው የምክክር ባህል ኣንጻር ሲወዳደር እንኳ እጅግ ኋላቀር መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን??
“ብራናው ይገለጥ ተዘርግቶ በኣትሮኖሱ ላይ”::
1
በጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ባድዋ ጦርነት ዋዜማ ስለነበረው ምክር ያይን እማኝ ሆነው የተመለከቱትን ጽፈውልናል፡፡ልቀንጨበው፤
“ራስ(መኮንን)…መኳንንታቸውን ሰብስበው የጦር ምክር ተደረገ፡፡ ራስ ኣሉላም ምክሩ ላይ ነበሩ፡፡
ሌሊት ሲነጋጋ ሸለቆ ለሸለቆ ወርደን እግንቡ ስር ተጠግተን በመሰላል እየተንጠላጠልን ከምሽጉ ውስጥ ገብተን(ጠላትን) እንፍጀው መንገዱን የራስ ኣሉላ ሰዎች ይመሩናል ተባለና ተቆረጠ፡፡ ይህንን ምክር መኳንንቱም የጦር ኣለቆችም ባለሟሎቹም ወደዱት፡፡ ኣንድ ሰው ብቻ በማእረጉ ዝቅተኛ የሆነ(የደራሲው ወንድም ኣብዩ)እየተቃወመ ተናገረ፡፡
ይህ ምክር ትልቅ ጉዳት ያመጣል ሰራዊታችንም በከንቱ ያልቃል ይልቅስ ታግሰን ቀንና ሌሊት ዘብ እየጠበቅን ውሃ ከምሽጉ ውጭ መቅዳት እንዳይችል እናድርግ …”ብሎ ተናገረ፡፡
ቀኛዝማች በሻህ ያብዩን ነገር ክፍኛ ነቀፉት…”ኣንተ ወረቀት ሲጻፍ ትመክራለህ ፡፡ፈርተህ እንደሆነ እሰፈር ዋል ፡፡ እኛ በሾተል እየቀነጠስን እንደኣይጥ እንፈጀዋለን ኣሉ….“
…ኣብዩ ከምንም ኣልቆጠራቸውም ፡፡ በትእግስት መለሰላቸው፡፡”ሰራዊታችን በከንቱ እንዲያልቅ በመደረጉ ኣዝናለሁ፡፡ እናንተ ስትሞቱ እኔ የቀረሁ እንደሁ ያን ጊዜ ፈሪ ተብየ እሰደባለሁ፡፡ “ይህ ተናገረና ወጣ፡፡”
(ኦቶባዮግራፊ፤ ገጽ 60)
የምክሩ ውሳኔ ምንም ይሁን ሰዎች በትልልቅ ኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰብስበው ይሟገቱ እንደነበር እንረዳለን ፡፡ በምክሩ ላይ የተለያየ ማእረግ ያላቸው ብቻ ሳይሆን የተለያየ ኣመለካከት ያላቸው ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ በምክክሩ ኣብላጫውን ውሳኔ መቃወም ብቻ ሳይሆን ስብሰባ ረግጦ መውጣትም ይታወቅ ነበር ማለት ነው(ይህን ተናገረና ወጣ“ ተብሎ የተጻፈለትን ኣብዩን ኣስታውሱ )
2
ፕላውደን የተባለ የንግሊዝ ተጓዥ፤ በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ በጉድሩ(ወለጋ)የተመለከተውን የሪፐብሊክ ኣስተዳደር እያደነቀ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፡፡
•”ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ስለሚኖረው ጉዳይ የሚወሰነው በጉባኤ ነው፡፡ ባደባባዩ ጉባኤ ለመታደም የሚፈልግ ሰው ሁሉ ክብ ሰርቶ ጦሩን ተደግፎ ከብቦ ቆሞ ይመለከታል፡ ፡ ሽማግሌዎች በሚያስደንቅ መንገድ ተራቸውን እየጠበቁ በሰላምና በጦርነት ዙርያ ይከራከራሉ።“
በራስ መኮንን የሸማ ድንኳን ውስጥ እና በጉድሩ መስክ ላይ የታየው ክርክርና ሙግት ፤ በዛሬው ፓርላማ ውስጥ ይታያል?ያለፈውን ስርኣት የመናፈቅ መብት በህገ መንግስቱ ይካተትልንማ!
ዲሞክራሲ ሂደት ነው ይባልልኛል፡፡ ሊሆን ይችላል፡፡ ባገሬ ግን እንኳን ሲሄድ ሲንፏቀቅ ኣይታየኝም፡ ፡ የሚሄድ ቢሆን ኖሮ ከቀደምቶቻችን ውጥን ላይ ተነስቶ ዛሬ ትልቅ ደረጃ ደርሶ እናየው ነበር፡፡ የሚታየኝ ወንበር ላይ ተቸክሎ በድሃ እንባ የተቦካ እንጀራ የሚበላ ሰው ብቻ ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ሳይወጡ ሳይወርዱ ቀኝ እጃቸውን ብቻ እያወጡ እያወረዱ እንጀራ የሚበሉበት ቤት፤ “ የተወካዮች ምክር” ቤት መባሉ ያስቃል፡፡ ምናልባት” የተቸካዮች ምክር ቤት “ የሚለው ስም ይመጥነው ይሆን?

7.5 million going hungry as Ethiopia crisis worsens

Addis Ababa (AFP) – The number of hungry Ethiopians needing food aid has risen sharply due to poor rains and the El Nino weather phenomenon with around 7.5 million people now in need, aid officials said Friday.The number of hungry Ethiopians needing food aid has risen
That number has nearly doubled since August, when the United Nations said 4.5 million were in need — with the UN now warning that without action some “15 million people will require food assistance” next year, more than inside war-torn Syria.
“Without a robust response supported by the international community, there is a high probability of a significant food insecurity and nutrition disaster,” the UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs, OCHA, said in a report.
The UN children’s agency, Unicef, warns over 300,000 children are severely malnourished.
The Famine Early Warning Systems Network (FEWS NET), which makes detailed technical assessments of hunger, predicted a harvest “well below average” in its latest report.
“Unusual livestock deaths continue to be reported,” FEWS NET said. “With smaller herds, few sellable livestock, and almost no income other than charcoal and firewood sales, households are unable to afford adequate quantities of food.”
Ethiopia, Africa’s second most populous nation, borders the Horn of Africa nation of Somalia, where some 855,000 people face need “life-saving assistance”, according to the UN, warning that 2.3 million more people there are “highly vulnerable”.
El Nino comes with a warming in sea surface temperatures in the equatorial Pacific, and can cause unusually heavy rains in some parts of the world and drought elsewhere.
Hardest-hit areas are Ethiopia’s eastern Afar and southern Somali regions, while water supplies are also unusually low in central and eastern Oromo region.
Food insecurity is a sensitive issue in Ethiopia, hit by famine in 1984-85 after extreme drought.
Today, Ethiopia’s government would rather its reputation was its near-double-digit economic growth and huge infrastructure investment — making the country one of Africa’s top-performing economies and a magnet for foreign investment.
Still, nearly 20 million Ethiopians live below the $1.25 poverty line set by the World Bank, with the poorest some of the most vulnerable to weather challenges.
Ethiopia’s government has mobilised $33 million (30 million euros) in emergency aid, but the UN says it needs $237 million.
Minster for Information Redwan Hussein told reporters at a recent press conference that Ethiopia is doing what it can.
“The support from donor agencies has not yet arrived in time to let us cope with the increasing number of the needy population,” he said.