Saturday 7 October 2017

Esat

#Esat

ሰበር ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ስልጣናቸዉን በፍቃዳቸዉ ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸዉን አዲስ እስታንዳርድ ዘገበ ፡፡
ለአባዱላ ስልጣን መልቀቅ ዋነኛዉ ምክንያት ከ150 ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች የተፈናቀሉበት በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተዉ የሰሞኑ ግጭት መፍትሄ ሊያገኝ አለመቻሉ ነዉ ተብሏል ፡፡
በዚህ ምክንያት ባለፉት ሳምንታት አፈ ጉባኤዉ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ጋር ከፍ ያለ መከራከር ዉስጥ ገብተዉ መሰንበታቸዉንም ጋዜጣዉ አስነብቧል ፡፡ በተያዘዉ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮቶኮል ሹምና አንድ ብርጋዴር ጀኔራል ስርዓቱን መክዳታቸዉ ይታወቃል ፡፡
Sat 07 Oct 2017