Monday 20 June 2016

የወያኔ መንግስት በሳይበር ጥቃት የተነሳ ከ 1 ቢሊዮን በላይ ብር ከሰርኩ አለ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋዊ ከትናንት በስቲያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል በአገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ሲሆን መንግስትንም ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርጐታል፡፡  ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጅግጅጋ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረርና ድሬደዋ ከተሞች  በተካሄደ አሰሳ፣ 400 የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች የተያዙ ሲሆን መሳሪያዎቹ ከ8 እስከ 720 ሲም ካርዶችን የመጠቀም አቅም ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል፡፡  46  ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በመንግስት ላይ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ማድረሳቸውን አስታውቋል፡፡
ለወንጀሉ መባባስ ምክንያቶች ናቸው ተብለው ከተጠቀሱት መካከል የቴክኖሎጂ መወሳሰብ፣ የባለድርሻ አካላት ንቃተ ህሊና ማነስ፣ የሲም ካርድ፣ የቮቸር ካርድና የኢቪዶ አገልግሎት ሽያጭ ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር አለመተሳሰር ይገኙበታል፡፡
በአገሪቱ የሚፈፀሙ የሳይበር ጥቃቶችን የመለየት፣ የመመከትና ምላሽ የመስጠት ተልዕኮ የተሰጠው “ኢትዮ ሶርት” የተባለ ማዕከል ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን የገለፀው የኤጀንሲው ሪፖርቱ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 165 የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸውንና ማዕከሉ ጥቃቶቹን ማክሸፉን ጠቁሟል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሳይበር በአገራችን ከዋና ዋና ወንጀል መፈፀሚያ ስልቶች አንዱ መሆኑን ሪፖርቱ ጠቅሶ፤ ይሄንን ለመከላከል የሚያስችል የሳይበር ወንጀል ህግ መፅደቁን አመልክቷል፡፡ የአገሪቱን የኤሌክትሮኒክስ ንግድና የኤሌክትሮኒክስ አስተዳደር አገልግሎቶች ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ የዲጂታል ፊርማ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ከመንግስት ባንኮችና ከተወሰኑ ተቋማት በስተቀር አብዛኛዎቹ የመንግስት ተቋማት የሳይበር ደህንነት ጉዳይን የተቋማቸው የስትራቴጂክና ኦፕሬሽናል አመራር አካል አድርገው እንደማይወስዱት ያመለከተው ሪፖርቱ፤  ለቁጥጥር አመቺ ያልሆኑ ሥርዓቶችን ስለሚዘረጉ በአገራዊ ደህንነት ላይ ስጋት እየፈጠሩ ነው ብሏል፡፡

መንግስቱ ኃይለማርያም ደርግ ከሱዳን ጋር በድንበር ጉዳይ የተፈራረመው ሰነድ የለም አለ

ሰሞኑን የወያኔወች ተላላኪ ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳን ጋር በድንበሩ ጉዳይ እየተዳደረና ተግባራዊ እያደረገ ያለው የቀድሞወች የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት እና የደርግ መንግስት ተፈራርመውት የነበረውን ነው ብሎ ተናግሮት የነበረውን አስመልክቶ የደርግ መንግስት ከሱዳን ጋር ምን የተፈራረመው ነገር አለ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ መንግስቱ ኃይለማርያም መስል ሲሰጡ ምንም የተፈራረምነው ነገር የለም። ኃይለማርያም እና ወያኔ ውሸታሞች ናቸው። ደርግ ከሱዳን ጋር የተፈራረመው ሰንድ ካለ ለምንድን ነው ወያኔወች ሰነዱን ለህዝብ ይፋ የማያደርጉት ሲሉ መንግስቱ ኃይለማርያም መልሰው ጠይቀዋል።
መንግስቱ ኃይለማርያም ሰለ ኢትዮ፡ሱዳን ድንበር ጉዳይ የሰጠውን ቃለ መጠየቅ ሙሉውን ከዚህ ላይ ያዳምጡ