Monday 28 August 2017

ESAT News (August 28, 2017)

ESAT News (August 28, 2017) The illegal dumping of toxic along Ethiopia’s road construction routes is resulting in higher rates of child mortality and increased rates of diseases associated with exposure to toxins, according to early research by economists at Queen Mary University of London (QMUL) and Trinity College Dublin (TCD). The researchers were able to link increased rates of death and disease known to be associated with the effects of exposure to toxic waste and the construction of new roads, according to a QMUL news published last week.

ኢሳት ዜና ነሃሴ 22

ኢሳት ዜና ነሃሴ 22   2009 ቦንብ አፈንድታችሁል የተባሉ ወጣቶች አሁንም እየታሰሩ ነው
በባህር ዳር ከተማ የገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ከከተማዋ ፖሊሶች ጋር በመሆን የተለያዩ ወጣቶችን ቦንብ አፈንድታቸኋል በሚል ጥርጣሬ  አሁንም በማሰር እያሰቃዩ ነው፡፡የባጃጅ አሽከራካሪዎችን አሳድማችኋል በሚልም ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ ወጣቶች ከበርካታ ቀን ግርፋትና ስቃይ በኋላ በዚህ ሳምንት ተለቀዋል፡፡የገዥው መንግስት የደህንነት አባላት  የከተማዋን ወጣቶች በየሰበቡ በማሰር ከማሰቃትና ከማንገላታት የማይቆጠቡ ከሆነ ከባድ እርምጃዎችን በቅርቡ መውሰድ እንደሚጀምሩ በህቡዕ የተደራጁ የከተማዋ ነዋሪዎች አስጠንቅቀዋል
እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ህብረቱ በህቡዕ እንደሚንቀሳቀስና ህዝቡ ብቻውን እንዳልሆነ ለማሳየት እንጅ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን የሚገልጹት የህብረቱ አባላት፣  የከተማዋ ወጣቶች ርምጃ መውሰድ ከጀመሩ ጉዳዩ ሊከፋ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
በሌላ በኩል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጻፊዎች መረጃ እያወጡ ነው በሚል ምርምራ እና ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ ባለስልጣናት መረጃዎች በየጊዜው የሚወጣው በፕሬዚዳንቱ ጸሃፊዎችና ረዳቶች ነው በሚል ምክንያት ክትትሉ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

Sunday 13 August 2017

አሁን የደረሰን ዜና።



አሁን የደረሰን ዜና። 
ዛሬ ነሀሴ 7 ቀን 2009ዓ/ም በጥዋቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአስቸኳይ ተጠርቶ የተደረገው ስብሰባ ያለ ስምምነት ተበተነ ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በስብሰባው አሁን አሁንስ ግራ እየገባኝ ነው በማለት የተናገሩ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል። በ3 ጉዳዬች ለመወያየት የተጠራው ስበሰባ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባና አመራሮች ፣ የአድማ በታኝ ፖሊስ አመራሮች ፣ የክልል ፖሊስ ኮሞሽን አመራሮች ፣ የመከላከያና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፌዎች ተገንተዋል ። አጀንዳው የፀጥታው ሁኔታውን ማየት ፣ ሱቆቻቸው የታሸጉባቸው ሰዎች ጉዳይ ማየት ፣ ከአድማው ጋር በተያያዘ በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞችን መመልከት ነው። በመሆኑም አቶ ገዱ የዚህ ከተማ ጉዳይ ከእለት እለት ፀጥታው እየባሰበትና በተለይም ለመቆጣጠር እጅግ አስቸጋሪ የሆነ በተከታታይ የቦንብ ጥቃቶች መፈፀማቸው በኗዋሪውና በመንግስት አመራሩና ሰራተኛው ፍርሃትን እና ድንጋጤን እየፈጠረ ይገኛል ሁሉም አመራር በተሰማራበት የስራ ኃላፊነት ውሳኔ መስጠት አልቻለም ፣ ህብረተሰቡም ከመንግስት ከለላና ጥበቃ ካልተደረገልን ስጋት ውስጥ ገብተናል የማለት አዝማሚያዎች እየተፈጠሩ ነው በዚህ ከቀጠልን ህዝባችን እኛ የምንለውን መስማት በመተው ፀረ ሰላምና ፀረ ህዝቦች የሚሉትን መስማት ይጀምራል ፣ በአለፈው በነበረን ውይይት ምንም ዓይነት ተቃዋሚ የለም በሶሻል ሚዲያ በተጠራ አድማ ነው ሰው የተረበሸው ስንል አንዳንድ አመራሮች ስጋታቸውን ሲገልፁ መቀበል ሲገባን በግልባጩ እነሱን ምታውቁት ካለ ንገሩን እኛ የምናውቀው የለም ብለን አሸማቀናቸው ነበር ፣ ከዚያ በሚቀጥለው ቀን ኬላዎች ተቋቋሙ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል አሰማራን ፍተሻዎች ተደረጉ ሀምሌ 30 ቀን 2009ዓ/ም በከተማው ቦንብ ያፈነዱ አካላትን በቁጥጥር ስር አዋልን ብለን አወጅን ፣ አሁን ደግሞ በተጠና አይነት በትናንትናው ምሽት የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ። ስለሆነም አንድ የመንግስት ተቋም ሊላኛውን በጥርጣሪ እየተመለከተ መቀጠሉ ለችግር እያጋለጠን ይገኛል ፣ እርስ በርስ እንደአጋር ከመተያየት ይልቅ በጠላት አይን መተያየቱ እየጨመረ ነው የመጣው ፣ ስለሆነም እኔ በፀጥታው ዙሪያ ከመደብነው የሰው ኃይልና በጀት አኳያ እየተሰራው ያለው ስራ ከዚህ ግባ የማይባል ነው እኔ ግራ እየገባኝ ነው በማለት የተናገረ ሲሆን ፣ በፖሊስ በኩልም የከተማው ፀጥታ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ነው ጥምር ኮሚቴውም ስራውን በአግባቡ እየሰራ አይደለም በማለት ሃሳብ ሰጥተዋለ ፣ አድማ በታኝም እኛ የተሰማራነው እና ስልጠና የወሰድነው በአደባባይ ወጥቶ ሁውከትና ብጥብጥ በሚፈጥር እንጅ በበፀት ውስጥ ተቀምጦ አድማ ለሚያደርግ ምን ማድረግ እንዳለብን የምናውቀው ነገር የለም ፣ቦንቡን ለመቆጣጠር ከአንዴ 3 ጊዜ ፍተባ አደረግን ፣ኪላዎችን አቋቁመን ፍተሻ አደረግን አሁንም ኪላዎች አልተነሱም ስለዚህ መቆጣጠር አልቻልነም፣ ከሆነም የሳዓት እላፌ ታውጆ ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ካልተቻለ በስተቀር ሁኔታው አስቸጋሪ ነው በማለት ተናግረዋል፣ ከዚያም የመከላከያና የብሔራዊ መረጃ ኃልፌዎች ለችግሩ መባባስ ወደ ፖለቲካው አመራር እጣታቸውን ቀስረዋል፣ በዚህ ጊዜ የከተማው ከንቲባና ሊሎች የካቢኔ አባላት እኛን ቀድሞም የፀጥታው ጉዳይ አይመለከተነም ሊሎችን ስራዎችን ነው መስራት ያለብን ደግሞም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣት ጀምሮ እኛን በጀት ከመመደብ ያለፈ ስራ እዳንሰራ ተከልክለን እና ታዛዥ ሁነን ነው ያለነው በማለት ተናግረዋል። አጠቃላይ የነበረውን ውይይት በዚህ ፅሁፍ ማቅረብ ስለማይቻልና ዓላማውም ይህ ባለመሆኑ የተደረሰበትን ነጥቦች ብቻ እንግለፅላቹሁ ፣ኮንቲነሮችን አሽገን ተከራዬችን ብንጠራቸውም አንዳቸውም ብቅ አላሉም፣ ቀምተን ለሊላ እድንሰጥ በተሰጠው አቅጣጫም ለኮንቲነር ፈላጊዎች ሰብስበን ብናወያይም የታሸጉትን ኮንቲነሮች ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነ የለም ፣ ማሸጋችን ሊላ ችግር እየፈጠረ ነው ይህም ግብር አንከፍልም ብለዋል ፣ ከታሸጉ ሱቆች የሚበላሽና የምግብ ውጠፀቶች መኖራቸው ፣የመንግስት ተቋማት የሆኑ መብራትና ቴሌ ፣ ውሃ ልማት ቆጣሪ ማንበብ አለመቻላቸውና በተለይ በቴሌ በኩል የካርድ ሽያጭ ሙሊ በሙሉ ቁማል ማለት ይቻላል፣ በዚህ ከቀጠለ ባለንብረቶች ሊከሱን ወይም ሁኔታው ወደ አመፅ ሊያድግ ይችላል የሚል ሃሳብ ቀርባል ፣በሊላም በኩል ከአድማው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውና መፍቲሄ አለመሰጠቱ ችግር ሁኖብናል የሚሉ ሃሳቦች ተነስተው ያለመቋጫ ተበትነዋል። በአሁኑ ሳዓት ክልሉን ማን እንደሚመራው የማይታወቅበት ደረጃ ላይ ተደረሰ ሲሆን ህዝቡም ለለውጥ ቆርጦ መነሳቱ በገዥዎችና በሎሊዎች ላይ ከፍተኛ ጭንቀትን ጥሏል። ትግላችን አስከ ነፃነት ድረስ ነው!!! 
ድል የህዝብ ነው !!! 
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ።