Saturday 27 February 2016

የኦሮሚያን ክልል መስተዳደር የስራ ሂደት እና አስተዳደሩን በሳሞራ የኑስ የሚመራው የጦር ሃይሎች መምሪያ ተረከበው::

የኦሮሚያን ክልል መስተዳደር የስራ ሂደት እና አስተዳደሩን በሳሞራ የኑስ የሚመራው የጦር ሃይሎች መምሪያ ተረከበው::
#Ethiopia #Oromoprotests #TPLFArmy #MinilikSalsawi #RDH
የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር በሳሞራ የኑስ በሚመራው የሕወሓት ጦር ሃይሎች መምሪያ ስምንተኛ የምድር ጦር ዲቭዥን እንዲመራ እና በሙክታር ከድር የሚመራው መስተዳደር ስራ አስተዳደሩን እንዲያቆም ሲደረግ ከወያኔ አገዛዝ የወጣው መረጃ አጠቃላይ የኦሮሚያ ክልል ከሲቪል አስተዳደር ወደ ወታደራዊ አስተዳደር መሸጋገሩ ታወቀ።የካቲት 19 /2008 በከፍተኛ የወያኔ የጦር መኮንኖችና : የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘደንት በሆኑት በአቶ ሙክታር ከድር መካከል በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከሲቪል አስተዳሩ ቁጥጥር ውጪ በመሆኑ የማስተዳደሩ ኃላፊነቱ በስምንተኛው የምድር ጦር ዲቪዥን ስር በሚገኙ የምድር ጦር ብርጌዶች እንዲሆን መወሰኑ ታወቀ::የኦሮሚያን ክልል መስተዳደር የስራ ሂደት እና አስተዳደሩን በሳሞራ የኑስ የሚመራው የጦር ሃይሎች መምሪያ ተረክቦታል::
ይህንን ርክክብ በስብሰባው ላይ የተገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ሃሳቡን የተቃወሙ ቢሆንም የሚሰማቸው ጠፍቶ ውሳኔው መወሰኑ ታውቋል ።ከፍተኛ ሀይል በመጠቀምና ህዝቡን በመጨፍጨፍ ተቃውሞን ለማስቆም ታስቦ የተወሰነ ነው በተባለለት በዚህ ውሳኔ ቀድሞም ለይስሙላ እንደነበር የሚታወቀው የነ አቶ ሙክታር ስልጣን ሙሉ ለሙሉ ተቀምቶ በወያኔዎች ለሚመራው በስምንተኛው የምድር ጦር ስር ለሚገኙ የምድር ጦር ብርጌዶች ተላልፏል ።
ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ቀጥቅጬ እገዛለው በሚል ያረጀ ያፈጀ እሳቤ እየተንቀሳቀስ ያለው የወያኔ መንግስት ያሰበው ጭፍጨፋ እንዳይሳካ መላው የኦሮሞ ህዝብና ሌሎች ሃገር ወዳድ ዜጎች በአንድነት በመቆም በቃህ ሊሉት ይገባል በማለት አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::

No comments:

Post a Comment