Wednesday 13 May 2015

የብሄራዊ ደህንነት መረጃ ሃላፊዎች ጥብቅ ፍተሻ እንዲካሄድ አዘዙ፤

ኢሳት ዜና ፦ ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ «ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት ጠባቂዎች ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር እንዲያደርጉ” ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
እንዲህ አይነት ትዕዛዝ ተላልፎ እንደማያውቅ የሚናገሩት ምንጮች፣ ትዕዛዙ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ረብሻ ሊፈጠር ይችላል ከሚል ስጋት ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች አስተያየታቸውን ቢሰጡም፣ ትዕዛዙ በኢህአዴግ ባለስልጣኖች ላይ ሳይቀር መተላለፉ ውሳኔው ከመጪው ምርጫ ጋር ብቻ ያልተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል። የደህንነት ሰራተኞች ለመስሪያ ቤት ሃላፊዎች ብቻ ሳይሆን ትዕዛዙን ለጥበቃ ሃላፊዎችም እየሰበሰቡ በመናገር ላይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment