Wednesday 3 May 2017

#Ethiopia :

#Ethiopia : ወጣቱ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል።አናስመስል ።አናሾክሹክ ።የትውልዱ ክሽፈት የኛ የጥላቻ መርዝ መሆኑን መዘንጋት ከሃገር ክሕደት አይተናነስም። ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል ፍቅር ይገዛናል ካልን በጋራ ተያይዘን ልንታገል ይገባል። ከሃገራቸው ጉዳይ የሚገፉ ሰዎች ለውጡን ለማደናቀፍና ተቃራኒውን ጎራ ለማለምለም ግንባር ቀደም ናቸው ስለዚህ ሃገር ወዳዶችን አንግፋቸው። ስለውነት እንታገል አናስመስል።መምሰል ክፉ በሽታ ነው ።ያልሆኑትን ሆኖ ለመታየት መሞከር ዕውነተኛ ማንነትን ማጣት ከመሆኑም በተጨማሪ የተነቃለታ ትልቅ ኪሣራ ያስከትላል፡፡ ወገን የሚመስሉን ወገኖችም ቢሆኑ “ከጠላጥ ውሰድ ወደ ዘመድህ ዞረህ ጉረስ” የሚለውን ተረት አሳምረው ያውቁታል፡፡ ይህን አለማስተዋል የማታ ማታ ዋጋ ያስከፍላል ፤መሆንህ እንጂ፣ መምሰልህ፣ ከቶ ለኔ ምን ፋይዳ አለው፤ዓለምን ዓለም ያረጋት፣ መልክ ሳይሆን ማንነት ነው፥ የሚለውን ግጥም አለመዘንጋት ነው፡፡ሀገራችን ብዙ አስመሳዮችን አስተናግዳለች፡፡ ነገም ገና ብዙ ታስተናግዳለች፡፡ አስመስሎ ማደር ወይም አድርባይነት ጊዜያዊ ወረት ነው፡፡ ወረቱ ሲያልቅ “ጨዋታው ፈረሰ፣ ዳቦው ተቆረሰ” ማለት ግድ ይሆናል፡፡ የዚህ ዓይነት ጨዋታዎች ሲፈርሱ፤ በአፄ ኃይለሥላሴም፣ በደርግም፣ በኢህአዴግም ዘመን፣ ታዝበን አልፈናል፡፡ “ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መቅጠፍ አሾክሻኪውን ነው”የሚለው ለረዥም ጊዜ ስንሰማ የኖርነው ቀረርቶ ነው።ወጣቱ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል።

No comments:

Post a Comment