Friday 2 September 2016

በዛሬዋ እለት በአሁኑ ሰአት ማምሻውን የመንግስት አየር ሀይል ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች የወልቃይት እና የአርማጭሁ አንዳንድ አካባቢወችን እየደበደቡ ነው የሚል መረጃ እየወጣ ይገኛል።

በዛሬዋ እለት በአሁኑ ሰአት
ማምሻውን የመንግስት አየር ሀይል ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች የወልቃይት እና የአርማጭሁ አንዳንድ አካባቢወችን እየደበደቡ ነው የሚል መረጃ እየወጣ ይገኛል።ይህ የመንግስት እኩይ ተግባር ያስቆጣቸው ያከባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞዋቸውን በጩኸትና በዋይታ በመግለፅ ላይ ናቸው ተብሎዋል።
ሕዝቤ ሆይ ያለን ብቸኛውና የመጨረሻው አማራጭ ራሳችንን ለማዳንም ሆነ ለመከላከል ጫካ ገብቶ ይሄንን አረመኔ ጠላት የሆነ መንግስት ተፋልሞ መጣል ብቻ ነው።
ተነስ አማራ ለወገንህ ድረስ!

በአዲስ አበባ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል

ዐርብ ነሐሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ ውስጥ በቤት ውስጥ በመቀመጥ መንግስትን የመቃወም ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የሃይማኖት አባቶች ለመንግስት ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አሥራ አምስት ቀናት መንግስት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በማዘጋጃ፣ በክፍለ ከተሞችና በወረዳወች የእያንዳንዱን ሃይማኖት ቤተ አምልኮ መሪዎችን በመሰብሰብ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
የውይይቱ ርዕስ ወቅታዊ ጉዳይ የሚል ነው
የመጀመርያው የውይይቱ ትኩረት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ክፍል ውስጥ በየቤተክርስቲያኑ አሸባሪዎች በሃይማኖት ስም በመንግስት ላይ ለአመጽ እያስተባበሩ ስለሆኑ ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር ልንከላከላቸው የምንችልበት ሁኔታ መፍጠር አለብን የሚል ነው፡፡
በአንፃሩ ሌሎች ቤተ እምነቶች የተጠሩት ጉዳዩን አጠቃላይ የሃማኖት አባቶች ጉባኤ ለማስመሰል እንደሆነ ታምኖበታል፡፡
ለጥያቄው የኦርቶዶክስ ካህናት በየሥፍራው የሰጡት ምላሽ ተመሳሳይ በመሆኑ መንግስት የካህናቱም እጅ በአመጽ እንቅስቃሴው ውስጥ ሳይኖርበት እንደማይቀር እንዲጠራጠር አድርጎታል፡፡ ሁሉም የመለሱት የሰንበት ትምህርት ክፍል በቁጥጥራችን ሥር ያለ አገልግሎት ሳይሆን የራሱ መዋቅር ያለው በመሆኑ ራሱ ይጠየቅበት እንጂ እኛን አይመለከተንም የሚል ነበረ፡፡
ሁለተኛው መንግስት ያቀረበው የሰላም ጉዳይ የሁላችን የጋራ ጉዳይ ስለሆነ የሃይማኖት አባቶች ስለ ሰላም ከወትሮ በተለየ ሁኔታ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከወትሮ የተለየ ስንል የአገሪቱን ሰላም የሚያውኩትን እስከ መጠቆም ድረስ ማለት ነው ብሏል፡፡
ይህ ሁሉም ተሰብሳቢ ከስብሰባው ከወጣ በኋላ በጣም ያነጋገረ ጉዳይ ሲሆን መንግስት የሃይማኖት ተቋማትን የስለላ ማዕከላት ሊያደርግ አለ እፍረት መነሳቱ ነው፡፡
የሃይማኖት አባቶቹ የአዲስ አበባ ሕዝብ በቤት ውስጥ በመቀመጥ ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በማንሳት እኛም ከቤታችን ካልወጣን በመንግስት ላይ ተቃውሞ እንዳለን ተደርጎ እንዳይታሰብ ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሕዝቡ በሙሉ በማይወጣበት አደባባይ መውጣት እስከሞት ድረስ ሊያስከፍለን ይችላል፡፡ በማናቸው ሰዓት ጥቃት ሊደርስብን እንደሚችል ስለማናውቅና መንግስት ቀንና ሌሊት ልጠብቀን ስለማይችል ራሳችንን ለማዳን ቤታችንን ዘግተን መቀመጥ ግዴታ ይሆንብናል ብለዋል፡፡
የእህል ገበያ የተወደደው ሰዎች በቤት የመቀመጥ አድማ ለማካሄድ እየገዛ በመሆኑ እንደሆነ የጠቆሙት አባቶች መንግስ እንዴት ሊያስቆም እንደሚችል ጠይቀዋል፡፡
መንግስት የእህል ዋጋ የተወደደው በረብሻው ምክንያት እህል አይገባም የሚል የተሳሳተ ወሬ ስለተነዛ የተፈጠረ ችግር ስለሆነ ችግሩን ለመፍታት ከነጋዴው ኅብረተሰብ ጋር እየተወያየን ነው ከሚለው በቀር በቤት ውስጥ በመቀመጥ ለሚገለጸው ተቃውሞ ለመከላከል መውሰድ የሚገባው ምን አማራጭ እንዳለው መግለጽ አልቻለም፡፡