Sunday 14 December 2014

በቅስቀሳው ወቅት የታሰሩት አመራሮችና አባላት አሁንም አልተፈቱም

ነገረ ኢትዮጵያ
10687129_627440187381643_6931792570194490039_nለ24ቱ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ ህዝብ ግንኙነትና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ፣ ባህረን እሸቱ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊ እንዲሁም ሲሳይ ዘርፉ እስካሁን ድረስ አልተፈቱም፡፡ ባህረን እሸቱና ማቲያስ መኩሪያ ከ30 በላይ እስረኞች ሶስት በአራት በሆነ ክፍል ታጭቀው በሚታሰሩበት ወረዳ 9፤ እንዲሁም ሲሳይ ዘርፉ ላዛሪስት በሚባል እስር ቤት ታስረው የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገልጾአል፡፡
ሶስቱም ታሳሪዎች ‹‹ለህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ በመቀስቀስ›› በሚል ክስ ቀረበባቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታሰሩት አመራሮች፣ አባላትና ተሳታፊዎች እነዚህ እስረኞች ላይ ከቀረበው በበለጠ ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› በሚል ክስ ተከሰው 14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ከተሰጠባቸው በኋላ ቀድመው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡

በአዳር ሰልፉ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ቡልቻ አባ ኑራ አንዱ ነው፡፡ ይህ ከተደበደበ ከ8 ቀን በኋላ የተነሳ ፎቶ ግራፍ ነው፡
SOURCE 
http://www.zehabesha.com/

No comments:

Post a Comment