Wednesday 17 May 2017

ይድረስ ለአረናው አብረሀ ደስታ:- አብረሀ ደስታ አንተን ስንወድህ ትግሬ ሆነህ ፣ ቴድሮስ አድኃኖምን ስንቃወመው ለምን በትግሬነቱ? – ካሳሁን ይልማ



ሕዝብ ላንተ አክብሮትና ፍቅር የሰጠው ያንተን ዘር ቆጥሮ አይደለም፤ ለሀገርህ እና ሕዝብህ መብት ተሟጋች ነህ ብሎ እንጂ። አንተ ግን ዛሬ ዘረኝነትን፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትን፣ ግፍን፣ ውሸትን... ሲዘሩ ለነበሩት ቴድሮስ ጥብቅና ቆመህ ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ደግፉ ትለናለህ። የሚቃወሙትን "ዘረኛ" ትላለህ።"ፓርቲና ግለሰብ ለዩ" ብለህ የፖለቲካ ሀሁ ልታስተምረን ትወተረተራለህ። ፓርቲ በሰው የተፈጠረ ሳይሆን ከሰማይ የወረደ ይመስል።ህወሓትን ከእነ ቴድሮስ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ ሳሞራ፣ ስብሐት ነጋ ፣ ... ስንለያየው ምን ይፈጠራል? እስኪ ንገረን:: ፓርቲው ምን ተብሎ ይጠራ? እነሱስ?

No comments:

Post a Comment