Thursday 14 July 2016

ሰበር ዜና. . . . . የህወሃት ብሐራዊ መረጃ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብቶአል።

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የእስራኤል ከፍተኛ ባልስልጣኖችን ለማዉጣት ከእስራኤል ሔለኒክ አየር ሐይል የልዩ ሐይል ( SPECIAL FORCE ) አባላትን የያዘ የጦር ጀቶችና አፓቼ ሄሊኮፍተሮች ( Apache Helicopters ) ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የተጠየቀዉ የወያኔዉ ብሔራዊ ደህንነት አመጽ በተቀሰቀሰባቸዉ የጎንደር አካባቢዎች ሰላም ሰፍሮዋል የሚል የተዛባ ማስተባበያ እየሰጠ ይገኛል።
ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ መንስኤ የሆነዉ የብሔራዊ መረጃ ሌሎች የታጠቁ ተጨማሪ የደህንነት አፋኝ ሐይሎች ህዝቡን አመሳስሎ ሊያስገባ መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆንበተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ የደህንነት ከፍተኛ አመራሮች አስተዳደሮችና ቁልፍ የስለላ ግለሰቦች ጎንደርን ለቀዉ እንዲወጡ ትእዛዝ ሲያስተላልፍ ህዝባቸዉ ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ለክክሉ የመከላከልና ዘመቻ ስምሪት ክፍል ትእዛዝ ቢተላለፍም የመከላከያ የጦር አባላትና፣ የአካባቢ ሚሊሻዎች እንዲሁም የክልሉ የፖሊስ አባላት አንዳች ጥይት እንደማይተኩሱና ህዝቡ ላይ ለሚወሰድ ማንኛዉንም አይነት እርምጃ የመከላከል ግዴታቸዉን እንደሚወጡ ለመረጃ ድርጅቱ በድፍረት ገልጸዋል።
በተያያዘ ሁኔታ አጋጣሚዉ የሰመረላቸዉ የዉስጥ አርበኞች በተጠናከረ መልኩ ህዝብን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የነበሩ አፋኝ ግለሰቦችን እያሳደዱ በማደን ላይ መሆናቸዉን የአርበኞቹ ምንጭ ጠቅሰዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
( ጉድሽ ወያኔ )
,
Aseged Tamene photo

No comments:

Post a Comment