Sunday 28 February 2016

በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ተቃውሞ ተሰምቷል::ተቃውሞውን አትኩሮት ለማሳጣት እና ለማጣጣል የሚደረጉ ሙከራዎች አልተሳኩም::




Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች በወያኔው አገዛዝ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በመቀጠል በዛሬው እለት በሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች እንዲሁም በበደኦ እና በቦኬ ጣቆ ከተማ በዳሮ ላቡ ሳኪና ከተማ ተቃውሞ ሲሰማ ውሏል::በወለጋ አርሲ እና ሸዋ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ የዋለ ሲሆን የአግኣዚ ጦር ወታደሮች ነዋሪዎችን ሲያንገላቱ ሲያዋክቦ ተስተውሏል:: እንዲሁም በየከተማው ያሉ መምህራ እና የልማት ሰራተኞችን በወያኔ የደህንነት ሃይሎች እይታ ስር ሲከታተሉ የዋሉ ሲሆን ወያኔ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ መቆጣጠር እንዳልቻለ እየታየ ይገኛል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በየአከባቢው ለግድያ እና አፈሳ የተመደቡ የአግኣዚ ወታደሮች ኢላማቸው በክልሉ ፖሊሶች ላይ በማድረግ በምእራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ውስጥ በአጋዚ ወታደር አደም ጫላ የተባለ አንድ ፖሊስ የተገደለ ሲሆን ሌላ ፖሊስ ደግሞ ቆስሎ ሆስፒታል ይገኛል ።የአግኣዚ ጦር በተሰጠው መመሪያ መሰረት በልማት ሰራተኞች በመምህራን እና በክልሉ ፖሊሶች ላይ የጭካኔ እርምጃ መውሰድ ቀጥሏል::
የኦሮሞ ሕዝብ የመብት ጥያቄ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋትን ተከትሎ በተቃውሞ ትግሉ መቀጣጠል ከጀመረ ጀምሮ የሕዝብን ንቅናቄ የራሳቸው ለማድረግ የሞከሩ እንዲሁም ትግሉን አሳንሶ እና አጣጥሎ ለማሳየት የተደረጉ ጥረቶች ከዛም ባለፈ ትግሉ አትኩሮት እንዳያገኝ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሊነሳ ነው ጦሩ ድንበር ተጠጋ ሲሉ የነበሩ የባዶ ፕሮፓጋንዳ ሙከራዎች በሙሉ መክሸፋቸውን በገሃድ እያየን እንገኛለን::የኦሮሞ ሕዝብ መብቴ እስካልተከበረ ድረስ ትግሉን አላቆምም ከማለቱም በላይ በዚህ የትግል ሂደት የተገደሉ ንጹሃንን አላማ ግብ ለማድረስ ትግሉን ቀጥሎ ይገኛል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment