Thursday 5 November 2015

በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ (ወለላዬ)


Patriotic Ginbot7 event in Sweden
አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ
ቅዳሜ ኦክቶበር 31 -2015 (ጥቅምት 20 – 2008 ዓ.ም ) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል።በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተና አመራር ናቸው።
Patriotic Ginbot7 event in Sweden
አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ
ዝግጅቱ ረፋዱን 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን አቶ ጌታሁን ማሬ የዝጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የስዊድን የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ዘለሌ ፀጋ ሥላሴን ስለዝግጅቱ ገለጻ እንዲያደርጉና ዝግጅቱንም እንዲመሩ ጋብዘዋል። አቶ ዘለሌ በበኩላቸው የከተማው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ያለበትን ሁኔታ ገልጸው እንግዶቹንም በማስተዋወቅ አቶ አበበ ቦጋለና አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር እንዲያደሩ ጋብዘውል።
Patriotic Ginbot7 event in Sweden
አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ
አቶ አበበ በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት ሰባት እየሰራ ስላለው የስራ ክንውን እቅድና አላማ እንዲሁም ደጋፊዎቹና አባላቶቹ እያደረጉ ስላሉት እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ቸኮል ጌታሁን በበኩላቸው በኤርትራ ቆይታቸው ወቅት ስለተመለከቱት የአርበኛው ቆራጥነትና የአላማ ጠንካራነት የገለጹ ሲሆን በአሁን ሰዓት የድሮ ጀግናችን ስም በመጥራት የምንቀመጥበት ጊዜ ሳይሆን እኛው እነሱን ተክተን በጀግንነት ስማችን ማስጠራት የሚገባን ጊዜ ነው በማለት ደጋፊውንና አባላትን የሚአበረታታና የሚነሳሳ መል ክት አስተላልፈዋል።
Patriotic Ginbot7 event in Sweden
ለጨረታ የቀረበው ምስል
ከሁለቱ አመራሮች ንግግር በኋላ ተሰብሳቢው ሰው ጥያቄ እንዲያቀርብ ተጋብዞ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል። እንዲሁም ንቅናቄውን በተመለከተ ግልጽ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በመቀጠል « በደል ይረሳል ወይ?» የሚል ግጥም በማራኪና በወለላዬ ከቀረበ በኋላ የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታ ተደርጓል። ለጨረታ የቀረበው የንቅናቄው ሊቀመንበር የሆኑት የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ቆራጡ አርበኛ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሚመሯቸው አርበኞች ጋር ሆነው የሚታዩበት «ላንቺ ነው ኢትዮጵያ » የተባለ ምስል ሲሆን ይሄው ምስል በግልና በቡድን ተጫርቶ ከፍተኛ ፉክክር ከተደረገ በኋላ በአንድ መቶ አራት ክሮነር( የስዊድን ገንዘብ ) የስዊድን የስደተኞች ማህበር አሸንፎ ምስሉን የግሉ አድርጎታል። ከዚህ ከጨረታ ከተገኘው ገንዘብ ሌላ ሁለት የቃል ኪዳን ቀለበቶች የመግቢያ ገንዘብ ሦስት መቶ ዶላርና ከእጣ የተሰበሰበ ገቢ ተገኝቷል።
Patriotic Ginbot7 event in Sweden
የጨረታው አሸናፊዎች
በወቅቱ በስደተኛ ማህበሩ አባላት ይደረግ የነበረው ተሳትፎ ዝግጅቱን አድምቆት አርፍዷል በጨረታው ጊዜም በማሃል እረፍት በሚደረግበት ወቅት የ/ሪት ሙሉቀን አማረ «ኢትዮጵያዊት ነሽ አትበሉኝ » የሚል ግጥምና የ/ሮ ውቤ ማሞ እንዲሁም የአቶ መብራቱ ፀሐዩ ቀስቃሽ ግጥሞች ቀርበዋል።
Patriotic Ginbot7 event in Sweden
የጨረታው አሸናፊዎች ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር

No comments:

Post a Comment