Tuesday 20 October 2015

የጨቋኘ ስርአት እድሜ በጣት መቆጠር የሚጀምረው ህዝብ ስርአቱን መፍራት ሲያቆም ነው !! የፈራ ይመለስ ጎንደር

በጎንደር ከተማ  የመስቀል በአልን  አስታኮ  የታየው ድንገተኛ ህዝባዊ ቁጣ የወያኔ ስርአትን ሲያስደነግጥ ለለውጥ ናፋቂዎች ታላቅ ብርታት ሆኗል።
”የፈራ  ይመለስ” የሚል ጽሁፍ የተጻፈባቸው  ቀይ ካኒቴራዎች  የለበሱ 500 የሚደርሱ የጎንደር ወጣቶች የመስቀል በአል ደመራ  የሚበራበትን አካባቢ መነሻ በማድረግ በጋራ ሲዘምሩ ታይተዋል ፣ ይህም ሁኔታ  በስርአቱ አምስት ለ አንድ ተጠፍንጎል የተባለው ህዝብ መካከል 500 የሚደርስ ካናቴራ ታትሞ ለህዝብ እሲኪደርስ ድረስ ከካድሬዎች ጆሮ አለመድረሱ እርግጥም ህዝብ ያልተቀበለው ስርአት ምንም አፋኝ ቢሆን የህዝብን ፈላጎት ፍጹም መገደብ እንደማይችል ማረጋገጫ የለም ለሚሉ ስዎች  እነሆ  ምስክር ብለናል ።
ትልቁ ጉዳይ ግን የአምስት ለአንድን ቀመር በዚህ ሁኔታ  ላይ ብንስራው  በ500 ሰው መሃል 100 ካድሬ ይኖራል ማለት ነው እነዚህ መቶ ካድሬዎች ይህን እቅድ ሳይደርሱበት ቀርተው ይሆናል የሚል መከራከሪያ  ነጥብ ሊኖር ቢችልም  ካድሬ ተብለው ደሞዝ እየበሉ የተገላቢጦሽ የወያኔን ስርአት ለማፈራረስ የሚተጉ የውስጥ አርበኞች አሉ የሚለው ሃሳብ እጅግ አሳምኖኛል ።
የፈራ  ይመለስ የሚለው መፈክር የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኘ ፅሁፍ እርእስ ስትሆን ከስርአቱ ጋርም ደም ያቃባችው መሆንዋን የሚረሳት ያለ አይመስለኝም ፣ ቁስሉ የተነካው ወያኔም  ቂሙን  ለመመለስ የጎንደርን ህዝብ በገፍ ለስቃይ እየዳረገ መሆኑን የዜና  ማሰራጫዎች በሰፊው ዘግበውታል
ወያኔዎች አንድ ግልጽ ያልሆነላችው ነገር ቢኖር   የመለስ ራእይ በዱላ  የሚስርጽ ቢሆን ኖሮ አማኙ በዝቶ ፌደራል  ፖሊስ  ድሮ ገና  ስራ በፈታ  ነበር ምክንያትም በመንገድ ያገኙትን ስው ሁሉ ልቀቅ ፣ ተበተን  እይሉ ያልቀለጠሙት ስው  አለ ብዬ አላምንም እና ።  ቅልጠማውም ጥብጠባውም ያልበገረው ህዝብ ሆ  ሲል ላየው ወደ ትግል ሜዳ እየሄዱ ያስመስላቸዋል ፣ እርግጥ ነው አንድነቱ እና ድፍረቱ  ቢበረታታም መጪውን አገር አቀፍ ትግል ውጤታማ ለማድረግ  ከሚያምነው የትግል  አጋሩ ጋር ተደራጅቶ ለቀጣዩ ወሳኝ ትግል ራሱን በመንፈስ በማዘጋጀት ለሚተላለፉ ህዝባዊ ተልእኮዎችን በተጠንቀቅ የመጠበቅ ስራ መተኮር ያለበት ወቅታዊ ተግባር መሆኑን ማስታውስ ያሻል እላለሁ ።
ድል ለኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ

No comments:

Post a Comment