Wednesday 16 September 2015

መለስ ዜናዊ ብርሃኑ ነጋ ቅዠት እንደሆነበት አለፈ፤ በረከት ስምዖንና ተከታዮቹ " የቅዠቱ ቫይረስ ተሸካሚዎች" ሆነው በቅዠት ማእበል እየተናጡ ነው። ብርሃኑ ነጋ ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል የሚወክል አንድ ምልክት ነው፤ በቅዠት ማእበል እየተናጡ ያሉ ሰዎች፣ ከማእበሉ ሊተርፉ የሚችሉት የህዝቡን የነጻነት ጥያቄ መመለስ ሲችሉ ብቻ ነው፤ ይህን ጥያቄ የብርሃኑን ስም በማጠልሽትም ሆነ ብርሃኑን ለማጥፋት ሚሊዮኖችን በመመደብ ማስቆም አይቻልም። አንዳርጋቸውን በማፈን ወይም አንዱአለምን ፣ አቡበክርን ፣ እስክድርን ወዘተ በማሰር ለመግታትም አይቻልም ምክንያቱም ዘረኞችንና አምባገነኖችን የሚያቃዠው የነጻነት መንፈስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሰፍሯልና። ይህን የሚያስቃዥ መንፈስ ለማስቆም የሚቻለው የኢትዮጵያን ህዝብ ጨርሶ ማጥፋት አልያም ጥያቄውን መመለስ ሲቻል ብቻ ነው።

No comments:

Post a Comment