Wednesday 27 January 2016

በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል።



በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል።
Negere Ethiopia's photo.
ፍ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ
*‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡
ዛሬ ጥር 17/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ዮናታን ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም በሚል የጠየቀበትን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለየካቲት 15/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋየ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡
ፖሊስ በአቶ ዮናታን ላይ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ ‹‹የቴክኒክ መረጃዎችን መሰብሰብ ይቀረናል፤ ያልተያዙ ግብረ አበሮችንም አሉ›› የሚል ምክንያት ማቅረቡን የተጠርጣሪ ጠበቃ ገልጸዋል፡፡
አቶ ዮናታን ተስፋየ በጠበቃ እና በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ እንደተከለከለና ከታሰረበት ክፍል መታፈን የተነሳ የጤና እከል ቢገጥመውም ህክምና እንዳላገኘ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን አድምጦ በጠበቃውም ሆነ በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ እንዲፈቀድለትና ህክምናም እንዲያገኝ ትዕዛዝ መስጠቱን ከጠበቃው ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ ዮናታን ከችሎት ሲወጣ በስፍራው ለነበሩት ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ያለውን ፍቅር ገልጾ ‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› በማለት ጮክ ብሎ ሲናገር ተደምጧል፡፡

No comments:

Post a Comment