Thursday 3 September 2015

አሳዛኝ…

ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት የሕጻን ልጅ አስክሬን በትላንትናው ዕለት ነበር በቱርኳ ቦድሩም ከተማ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ የተገኘው፡፡ ሕጻኑ ከቱርክ ወደ ግሪኳ ደሴት ኮስ በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ሰጥመው ከሞቱት ስደተኞች ጋር አብሮ እንደነበር ይገመታል፡፡
ክስተቱ እየተባባሰ ያለው የስደተኞች አበሳ የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል፡፡
በሚሰጥሙ ጀልባዎች ሳቢያ ከሚያልቁት ስደተኞችም በተጨማሪ፣ በተጣበቡት ጀልባዎች ውስጥ ታፍነውና ተረጋግጠው እንዲሁም በጀልባዎቹ መርዛማ ጭስ ታፍነው የሚሞቱትም ስፍር ቁጥር የላቸውም ነው የሚባለው፡፡

No comments:

Post a Comment