Sunday 27 September 2015

የዓመቱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ

pro.Brihanu
ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይገባዋል፦
ጀግኖቻችንን እናወድስ
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር የነበረው አሁን ደግሞ የአዲሱ የኢትዮጵያ አገር አድን የጋራ ንቅናቄ መስራችና ሊቀመንበር የሆነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እምዬ ኢትዮጵያ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ አምጣ ከወለደቻቸው ብርቅዬ የዘመናችን ጀግኖች ልጆቿ አንዱ በመሆን በኢሳት ቴሌቪዥን አገልግሎት የዓመቱ ምርጥ ሰው ተብሎ መመረጡ ከልብ አስደስቶኛል። ብዙዎቻችን ያልደፈርነውን የእንግልት፣ የረሃብ፣ የጥምና የህይወት መስዋዕትነት በመድፈር ሚሊዮኖች ከሚናፍቋት የምድር ገነት አሜሪካ ወደ ኤርትራ በረሃ ሲገባ በእውነት ነፃነቴን ያረጋገጥሁት ያኔ ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮው ምቹ ስፍራውን ለመልቀቅ የማይወድ ባህሪ ያለው ሲሆን ሁሉ ጊዜ ችግርን ፊት ለፊት ለመጋፈጥም ያለው አቅምና ወኔም ከሰው ሰው ይለያያል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ልዩ የሚያደርገው ባህሪው በአብዮቱ ዘመን ለዲሞክራሲ፣ ለፍትህና ለነፃነት መስፈን ብዙ ዋጋ የከፈለና እንደገናም በዘመነ ወያኔ በ1997 ዓ •ም ኢትዮጵያዊያንን አስተባብሮ የወያኔን ገመና ገልጦ በማሳየት ትውልዱን ለነፃነት ያነቃነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ከዚያም በኋላ በግፍ በስርዓቱ ወሮ በሎች የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ ተዘርፎ ጀግኖቻችን ወደ ወህኒ ሲወረወሩ አንዱ ነበር። ችግር የማይበግረው የኢትዮጵያውያን ነፃነት፣ ክብርና እኩልነት የሚያንገበግበው ታላቅ ምሁር ነው።
አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ስድሳ አመታት አምጣ ከወለደቻቸው ብርቅዬ ልጆቿ አንዱ የሆነውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን በአዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሆነን ክብር ለሚገባው ክብርን፣ ምስጋና ለሚገባው ምስጋናን እንሰጠዋለን። ብዙዎቻችን ከወሬ ባለፈ ያልሞከርነውን የትጥቅ ትግል ያስጀመረ የዘመናችን ታላቅ አርበኛ ስለሆነ ጎንበስ ብለን ክብር እንሰጠዋለን። እንደ እኛ የሚወዳት ሚስት፣ የሚሳሳላቸው ልጆች ያሉት ይህ ታላቅ ሰው አገሩንና ወገኑን ከሁሉ በላይ አስቀድሟልና በድጋሜ ክብር ይገባዋል እላለሁ።
ወያኔ በዚህ ሰሞን አንድን ተራ ንፍጣም ገሃዲ ከፍ ከፍ ማድረጓ ጀግናችን የፈጠረባት ጭንቄት መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ጀግኖቻችንን እናወድስ፣ ከጎናቸው እንሁን፣ ክብር እንስጣቸው።
በአጠቃላይ በአገር ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለማይቀረው ለውጥ ተዘጋጁ፣ ተነጋገሩ፣ አንገዛም በሉ። ወያኔ መውደቂያው ተቃርቧል ።
በድጋሜ ለጀግናችን ክብርና ሞገስ ይገባዋል።
ጀግኖቻችንን ስናወድስ የኢያሪኮ ቅጥር ይፈርሳል!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ድል ለኢትዮጵያ አገር አድን የጋራ ንቅናቄ

No comments:

Post a Comment