Friday 15 May 2015

ቆራጡ ታጋይ ማሙሸት አማረ ታፈነ

አሳዛኝ የእስራት ዜና 11212178_449222835253952_5616984280646183603_o
ቆራጡ ታጋይ ማሙሸት አማረ ታፈነ
ማሙሸት ትግል የጀመረው በ1984 ዓም ነው በ1980 ዎቹ ደብረብርሀን እስር ቤት ሰብረህ እስረኛ አስመልጠሀል ተብሎ ሞት ተፈርዶበት ከረጅም እስር በኋላ ተለቋል በ1997 ዓም ይሙት በቃ ተብሎ ተፈርዶበት እንደማንኛውም የቅንጅት አመራር በይቅርታ ተፈቷል እስከ 2003 ዓም የመኢአድ ከፍተኛ አመራር ነበር ከ2003 ዓም ጀምሮ ከፓርቲው በወንበዴዎች ተባረን ብንወጣም ባደረግነው እልህ አስጨራሽ ትግል ጥቅምት 28— 30 2007 ዓም መኢአድ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የመኢአድ ፕሬዝደንት ሆኖ ተመርጦ ነበር በምር በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ከፅ/ ቤት በፌደራል ፓሊስ መባረራችን ይታወቃል ።
ምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መስርተን እየተንቀሳቀስን ባለንበት ወቅት ዛሬ 2: 00 አካባቢ ከቤት ወደ ት/ቤት በመሄድ ላይ እያለ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ቴዲ ባር አካባቢ ሲቢል በለበሱ ደህንነቶች በቤት መኪና ታፍኖ ተወስዷል ። የኔም ሁኔታ ባያስተማምንም ሁኔታውን እየተከታተልኩ እመለሳለሁ

No comments:

Post a Comment