Saturday 16 May 2015

ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ነው& 1997 በትውስታ* ክዶ/ር ታደሰ ብሩ

ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ነው። ከዛሬ 10 ዓመታት በፊት ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ነበር። አይገርምም?
“የ1953ቱ የመግሥቱ ንዋይ መፈቅለ መግሥት ሙከራ ለ1966 ቱ ሕዝባዊ አብዮት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል” ሲሉ ሩቅ .. ሩቅ የነበረ እውነት አድርጌ ስቀበለው ኖረዓለሁ። በ53 እና በ66 መካከል ያሉት 13 ዓመታት ጥቂት መሆናቸውን የገባኝ ዛሬ ነው።
ይኸው እኔም ትናንትን የሆነ አስመስዬ የማወራው የ1977 ቱ ግንቦት 7ም ከተፈፀመ አስር ዓመታት አለፉ።
ግንቦት 7 ቀን 1997 በዚህ ሰዓት የነበርኩበት ስሜት ትናንትና ከነበርኩት ሁኔታ በላይ ይሰማኛል። እኔ የቅንጅት ታዛቢ በነበርኩበት ጣቢያ – በተለይ ደግሞ ድምፅ ሲቆጠር – ይሰማኝ የነበር የኃላፊነት ስሜት አሁንም አለ። የዚያን ምሽት አብሮኝ የነበረው የኢህአዴግ የምርጫ ታዛቢን እስከዛሬ አለማግኘቴ ይቆጨኛል። የዚያን ምሽት አልፎ አልፎ ብቅ ይሉ የነበሩ የኢህአዴግ ድምጾች ሳይቆጠሩ እንዳይታለፉ ተስፋ ቆርጦ የቆጠራዉን ክትትል ትቶት ከነበረው የኢህአዴግ ታዛቢ በላይ እኔ መባለቴን ዛሬ ሳስበው ይደንቀኛል። ስንለያይ እንደምንገናኝ እርግጠኞች ሆነን ነበር፤ ስለ ኢንተርፕሪነርሺፕ ስልጠናዎች ሳይቀር አውርተናል።
ባላፉት አስር ዓመታት የተማርኩት ሀቅ ግን ህወሓት ስልጣን ላይ እያለ ግንቦት 7 1997 የነበረኝ ስሜት መመለስ የማይችል መሆኑን ነው። የ53ቱ ዶፍ ዝናብ የ66ቱን የጎርፍ መጥለቅለቅ አመጣ፤ የ97ቱ ማዕበል ዛሬ ሊያሽረን እየተናወጠ ነው።
ለግንቦት 7 ዓመታዊ በዓል ብስራት እንዲሆን ቸር ወሬ የያዘ መግለጫን አያይዣለሁ። መልካም ትውስታ።

No comments:

Post a Comment