ኢሳት ዜና ነሃሴ 22 2009 ቦንብ አፈንድታችሁል የተባሉ ወጣቶች አሁንም እየታሰሩ ነው
በባህር ዳር ከተማ የገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ከከተማዋ ፖሊሶች ጋር በመሆን የተለያዩ ወጣቶችን ቦንብ አፈንድታቸኋል በሚል ጥርጣሬ አሁንም በማሰር እያሰቃዩ ነው፡፡የባጃጅ አሽከራካሪዎችን አሳድማችኋል በሚልም ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ ወጣቶች ከበርካታ ቀን ግርፋትና ስቃይ በኋላ በዚህ ሳምንት ተለቀዋል፡፡የገዥው መንግስት የደህንነት አባላት የከተማዋን ወጣቶች በየሰበቡ በማሰር ከማሰቃትና ከማንገላታት የማይቆጠቡ ከሆነ ከባድ እርምጃዎችን በቅርቡ መውሰድ እንደሚጀምሩ በህቡዕ የተደራጁ የከተማዋ ነዋሪዎች አስጠንቅቀዋል
እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ህብረቱ በህቡዕ እንደሚንቀሳቀስና ህዝቡ ብቻውን እንዳልሆነ ለማሳየት እንጅ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን የሚገልጹት የህብረቱ አባላት፣ የከተማዋ ወጣቶች ርምጃ መውሰድ ከጀመሩ ጉዳዩ ሊከፋ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
በሌላ በኩል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጻፊዎች መረጃ እያወጡ ነው በሚል ምርምራ እና ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ ባለስልጣናት መረጃዎች በየጊዜው የሚወጣው በፕሬዚዳንቱ ጸሃፊዎችና ረዳቶች ነው በሚል ምክንያት ክትትሉ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።
Monday, 28 August 2017
ኢሳት ዜና ነሃሴ 22
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment