Monday 7 September 2015

ሰላሳ ስድስት ቀን በፍርድ ቤት - ፍትህ ኖንቼ !!!! ግርማ ካሳ




ሰላሳ ስድስት ቀን በፍርድ ቤት - ፍትህ ኖንቼ !!!! ግርማ ካሳ
ዛሬ ሰኞ (ለጷግሜ 2ቀን 2007 ዓ/ም) የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች በፍቃዱ ዘ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩበትን 500ኛ ቀን ነው። በተለያየ ምክንያት ሲጓተት የነበረው የፍርድ ሂደትም የመጨረሻ እልባት ዛሬ ያገኛል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
ሆኖም ዞኢን ዘጠኞ አሁን ፍትህ ተነፍገዋል። ዛሬ ለሰላሳ ስድስተኛ ጊዜ ነበር ፍርድ ቤት የቀረቡት። ሆኖም በዳኞች አልተሟሉም በሚል ለመስከረም 27 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደገና ተሰጥቷቸዋል። ለሰላሳ ሰባት ጊዜ እንደገና ፍርድ ቤት ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።
ኢሕአዴግ አገሪቷን ላለፉት ሃያ አራት አመታት ሲገዛ የነበረ ድርጅት ነው። ባለስልጣናቱም በተለያዩ ጊዜያት "ሕግ ፣ ሕገ መንግስት፡ እያሉ ሲሰብኩና ሲለፍ ፉ ይደመጣሉ። ሆኖም በኢሕአዴግ ኢትዮጵያ የሕግ ስር፤ዓት ፍጹም የሌለበት፣ ዜጎች ፍትህ ማግኘት የማይችሉባት አገር እንደሆነች፣ የዞን ዘጠኞች አሳቂኝና አሳዛኝ የፍርድ ሂደት በግልጽ ለማሳየት ችሏል።
ዞን ዘጠኞች እርግጥ ነው፣ እስሩ በተራዘመ ቁጥር በነርሱና በቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና ጓደኞቻቸው ዘንድ ሕመም ቢፈጥርም፣ በወህኒ እየከፈሉት ያለው መስዋትነት ግን ፣ በአገሪቷ ያለውን መሰረታዉ ችግፍ ፍንትዉ ብሎ እንዲወጣ ለማድረግ ችሏል።

No comments:

Post a Comment