Wednesday 13 May 2015

ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት እነወይንሸት እስከ ግንቦት 24 ድረስ በእስር እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ ወስኗል

በዚህም መሰረት ዛሬ ወይም ነገ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይዛወራሉ ገዢው ፓርቲ እነወይንሸትን ለምን በእስር እንዲቆዩ እንደፈለገ ሀቅ ነው እነወይንሸት ከታሰሩ ምርጫውን ሲያጭበረብር ለምን የሚል ትውልድ በከተማው ሊኖር አይገባም
የወይንሸትን ጥንካሬ ደግሞ ገዢዎቻችን ጭምር ያውቁታል ወይንሸት ብቻዋን ከማንም በላይ የምርጫን ውጤት መወሰን የምትችል የዘመናችን ጅግና ነች
ወይንሸትን ከዚህ በፊት የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት የምትፈልጊውን ሀገር ቪዛ እንስጥሽና ከዚህ ሀገር ውጪ ሲሏት ሀገሬ ኢትዮጵያ ነው የኢትዮጵያን ቪዛ ስጡኝ አልላችሁም ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቪዛ ካርድ ላይ የታተመ ሳይሆን በኛ በልጆቿ ልብ ውስጥ ነው በማለት በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ጥርስ ውስጥ ገብታ ነበር
እውነት እውነት እላችሗለው ወይንሸትን ገዢው ፓርቲ በማሰሩ ወይኒ ምንም የምታጣው ነገር አይኖርም ምክንያቱም ባለመታሰሯ ያገኘችውም ምንም የለም

No comments:

Post a Comment