Wednesday, 22 November 2017

(ኢሳት ዜና - November 22, 2017)

(ኢሳት ዜና - November 22, 2017)
— በቀንጢቻ (ጉጂ ዞን) የተቃውሞ ሰልፉ ቀጥሎ ውሏል። ከአካባቢው ቲታኒየም የሚባል ማእድን እየወጣ መንግስት ተጥቃሚ ሲሆን በአካባቢው ግን ምንም አይነት መሰረተ ልማት የለም።
— የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በርካታ የኦሮሞ ተወላጆችን መግደላቸውን ተፈናቃዮች ገለጹ። "ሹፌሮችን ባረፉበት አልቤርጎ ነው ያረዷቸው፣ የተገደሉ ሰዎች በአንድ ጉድጓድ በዶዘር እየተገፉ ሲገቡ አይቻለው፣ የህወሃቱ ተወካይ ጉድጓዱን አስከፍቶ በአይኑ ተመልክቷል..."
— እስረኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና በአርበኞች ግንቦት 7 ስም የተከሰሱ እስረኞች በተሰጣቸው ቀጠሮ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።
— ሌሎችም ዜናዎች...

Saturday, 7 October 2017

Esat

#Esat

ሰበር ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ስልጣናቸዉን በፍቃዳቸዉ ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸዉን አዲስ እስታንዳርድ ዘገበ ፡፡
ለአባዱላ ስልጣን መልቀቅ ዋነኛዉ ምክንያት ከ150 ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች የተፈናቀሉበት በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተዉ የሰሞኑ ግጭት መፍትሄ ሊያገኝ አለመቻሉ ነዉ ተብሏል ፡፡
በዚህ ምክንያት ባለፉት ሳምንታት አፈ ጉባኤዉ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ጋር ከፍ ያለ መከራከር ዉስጥ ገብተዉ መሰንበታቸዉንም ጋዜጣዉ አስነብቧል ፡፡ በተያዘዉ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮቶኮል ሹምና አንድ ብርጋዴር ጀኔራል ስርዓቱን መክዳታቸዉ ይታወቃል ፡፡
Sat 07 Oct 2017

Monday, 28 August 2017

ESAT News (August 28, 2017)

ESAT News (August 28, 2017) The illegal dumping of toxic along Ethiopia’s road construction routes is resulting in higher rates of child mortality and increased rates of diseases associated with exposure to toxins, according to early research by economists at Queen Mary University of London (QMUL) and Trinity College Dublin (TCD). The researchers were able to link increased rates of death and disease known to be associated with the effects of exposure to toxic waste and the construction of new roads, according to a QMUL news published last week.

ኢሳት ዜና ነሃሴ 22

ኢሳት ዜና ነሃሴ 22   2009 ቦንብ አፈንድታችሁል የተባሉ ወጣቶች አሁንም እየታሰሩ ነው
በባህር ዳር ከተማ የገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ከከተማዋ ፖሊሶች ጋር በመሆን የተለያዩ ወጣቶችን ቦንብ አፈንድታቸኋል በሚል ጥርጣሬ  አሁንም በማሰር እያሰቃዩ ነው፡፡የባጃጅ አሽከራካሪዎችን አሳድማችኋል በሚልም ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ ወጣቶች ከበርካታ ቀን ግርፋትና ስቃይ በኋላ በዚህ ሳምንት ተለቀዋል፡፡የገዥው መንግስት የደህንነት አባላት  የከተማዋን ወጣቶች በየሰበቡ በማሰር ከማሰቃትና ከማንገላታት የማይቆጠቡ ከሆነ ከባድ እርምጃዎችን በቅርቡ መውሰድ እንደሚጀምሩ በህቡዕ የተደራጁ የከተማዋ ነዋሪዎች አስጠንቅቀዋል
እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ህብረቱ በህቡዕ እንደሚንቀሳቀስና ህዝቡ ብቻውን እንዳልሆነ ለማሳየት እንጅ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን የሚገልጹት የህብረቱ አባላት፣  የከተማዋ ወጣቶች ርምጃ መውሰድ ከጀመሩ ጉዳዩ ሊከፋ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
በሌላ በኩል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጻፊዎች መረጃ እያወጡ ነው በሚል ምርምራ እና ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ ባለስልጣናት መረጃዎች በየጊዜው የሚወጣው በፕሬዚዳንቱ ጸሃፊዎችና ረዳቶች ነው በሚል ምክንያት ክትትሉ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

Sunday, 13 August 2017

አሁን የደረሰን ዜና።



አሁን የደረሰን ዜና። 
ዛሬ ነሀሴ 7 ቀን 2009ዓ/ም በጥዋቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአስቸኳይ ተጠርቶ የተደረገው ስብሰባ ያለ ስምምነት ተበተነ ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በስብሰባው አሁን አሁንስ ግራ እየገባኝ ነው በማለት የተናገሩ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል። በ3 ጉዳዬች ለመወያየት የተጠራው ስበሰባ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባና አመራሮች ፣ የአድማ በታኝ ፖሊስ አመራሮች ፣ የክልል ፖሊስ ኮሞሽን አመራሮች ፣ የመከላከያና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፌዎች ተገንተዋል ። አጀንዳው የፀጥታው ሁኔታውን ማየት ፣ ሱቆቻቸው የታሸጉባቸው ሰዎች ጉዳይ ማየት ፣ ከአድማው ጋር በተያያዘ በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞችን መመልከት ነው። በመሆኑም አቶ ገዱ የዚህ ከተማ ጉዳይ ከእለት እለት ፀጥታው እየባሰበትና በተለይም ለመቆጣጠር እጅግ አስቸጋሪ የሆነ በተከታታይ የቦንብ ጥቃቶች መፈፀማቸው በኗዋሪውና በመንግስት አመራሩና ሰራተኛው ፍርሃትን እና ድንጋጤን እየፈጠረ ይገኛል ሁሉም አመራር በተሰማራበት የስራ ኃላፊነት ውሳኔ መስጠት አልቻለም ፣ ህብረተሰቡም ከመንግስት ከለላና ጥበቃ ካልተደረገልን ስጋት ውስጥ ገብተናል የማለት አዝማሚያዎች እየተፈጠሩ ነው በዚህ ከቀጠልን ህዝባችን እኛ የምንለውን መስማት በመተው ፀረ ሰላምና ፀረ ህዝቦች የሚሉትን መስማት ይጀምራል ፣ በአለፈው በነበረን ውይይት ምንም ዓይነት ተቃዋሚ የለም በሶሻል ሚዲያ በተጠራ አድማ ነው ሰው የተረበሸው ስንል አንዳንድ አመራሮች ስጋታቸውን ሲገልፁ መቀበል ሲገባን በግልባጩ እነሱን ምታውቁት ካለ ንገሩን እኛ የምናውቀው የለም ብለን አሸማቀናቸው ነበር ፣ ከዚያ በሚቀጥለው ቀን ኬላዎች ተቋቋሙ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል አሰማራን ፍተሻዎች ተደረጉ ሀምሌ 30 ቀን 2009ዓ/ም በከተማው ቦንብ ያፈነዱ አካላትን በቁጥጥር ስር አዋልን ብለን አወጅን ፣ አሁን ደግሞ በተጠና አይነት በትናንትናው ምሽት የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ። ስለሆነም አንድ የመንግስት ተቋም ሊላኛውን በጥርጣሪ እየተመለከተ መቀጠሉ ለችግር እያጋለጠን ይገኛል ፣ እርስ በርስ እንደአጋር ከመተያየት ይልቅ በጠላት አይን መተያየቱ እየጨመረ ነው የመጣው ፣ ስለሆነም እኔ በፀጥታው ዙሪያ ከመደብነው የሰው ኃይልና በጀት አኳያ እየተሰራው ያለው ስራ ከዚህ ግባ የማይባል ነው እኔ ግራ እየገባኝ ነው በማለት የተናገረ ሲሆን ፣ በፖሊስ በኩልም የከተማው ፀጥታ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ነው ጥምር ኮሚቴውም ስራውን በአግባቡ እየሰራ አይደለም በማለት ሃሳብ ሰጥተዋለ ፣ አድማ በታኝም እኛ የተሰማራነው እና ስልጠና የወሰድነው በአደባባይ ወጥቶ ሁውከትና ብጥብጥ በሚፈጥር እንጅ በበፀት ውስጥ ተቀምጦ አድማ ለሚያደርግ ምን ማድረግ እንዳለብን የምናውቀው ነገር የለም ፣ቦንቡን ለመቆጣጠር ከአንዴ 3 ጊዜ ፍተባ አደረግን ፣ኪላዎችን አቋቁመን ፍተሻ አደረግን አሁንም ኪላዎች አልተነሱም ስለዚህ መቆጣጠር አልቻልነም፣ ከሆነም የሳዓት እላፌ ታውጆ ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ካልተቻለ በስተቀር ሁኔታው አስቸጋሪ ነው በማለት ተናግረዋል፣ ከዚያም የመከላከያና የብሔራዊ መረጃ ኃልፌዎች ለችግሩ መባባስ ወደ ፖለቲካው አመራር እጣታቸውን ቀስረዋል፣ በዚህ ጊዜ የከተማው ከንቲባና ሊሎች የካቢኔ አባላት እኛን ቀድሞም የፀጥታው ጉዳይ አይመለከተነም ሊሎችን ስራዎችን ነው መስራት ያለብን ደግሞም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣት ጀምሮ እኛን በጀት ከመመደብ ያለፈ ስራ እዳንሰራ ተከልክለን እና ታዛዥ ሁነን ነው ያለነው በማለት ተናግረዋል። አጠቃላይ የነበረውን ውይይት በዚህ ፅሁፍ ማቅረብ ስለማይቻልና ዓላማውም ይህ ባለመሆኑ የተደረሰበትን ነጥቦች ብቻ እንግለፅላቹሁ ፣ኮንቲነሮችን አሽገን ተከራዬችን ብንጠራቸውም አንዳቸውም ብቅ አላሉም፣ ቀምተን ለሊላ እድንሰጥ በተሰጠው አቅጣጫም ለኮንቲነር ፈላጊዎች ሰብስበን ብናወያይም የታሸጉትን ኮንቲነሮች ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነ የለም ፣ ማሸጋችን ሊላ ችግር እየፈጠረ ነው ይህም ግብር አንከፍልም ብለዋል ፣ ከታሸጉ ሱቆች የሚበላሽና የምግብ ውጠፀቶች መኖራቸው ፣የመንግስት ተቋማት የሆኑ መብራትና ቴሌ ፣ ውሃ ልማት ቆጣሪ ማንበብ አለመቻላቸውና በተለይ በቴሌ በኩል የካርድ ሽያጭ ሙሊ በሙሉ ቁማል ማለት ይቻላል፣ በዚህ ከቀጠለ ባለንብረቶች ሊከሱን ወይም ሁኔታው ወደ አመፅ ሊያድግ ይችላል የሚል ሃሳብ ቀርባል ፣በሊላም በኩል ከአድማው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውና መፍቲሄ አለመሰጠቱ ችግር ሁኖብናል የሚሉ ሃሳቦች ተነስተው ያለመቋጫ ተበትነዋል። በአሁኑ ሳዓት ክልሉን ማን እንደሚመራው የማይታወቅበት ደረጃ ላይ ተደረሰ ሲሆን ህዝቡም ለለውጥ ቆርጦ መነሳቱ በገዥዎችና በሎሊዎች ላይ ከፍተኛ ጭንቀትን ጥሏል። ትግላችን አስከ ነፃነት ድረስ ነው!!! 
ድል የህዝብ ነው !!! 
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ።

Monday, 17 July 2017

ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው በእስር ሲሰቃዩ የነበሩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ሲል የቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት ሀምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ተከሳሾች ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብሎ የዋስትና መብታቸውን ከመቀበሉ በተጨማሪ ጉዳያቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ፣ ክርክሩ በቀደመው ችሎት እንዲቀጥል፣ የፍርዱ ሂደቱ እስኪያልቅ ከአገር እንዳይወጡ፣ ማረሚያ ቤቱም የፎቶ መራጃቸውን ለብሔራዊ ደኅንነት እንዲልክ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ በተጨማሪም አቤቱታ አቅራቢዎች በዝግ ችሎት መታየት የለበትም ብለው ያቀረቡትን ውድቅ አድርጎ በውሳኔው እንዲፀና በይኗል። ከሕዳር 08 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ያሳለፉት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ድረስ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ይውጡ አይውጡ አልታወቀም።

Wednesday, 14 June 2017

US State Department Issues Another Travel Warning for Ethiopia

The Department of State warns U.S. citizens of the risks of travel to Ethiopia due to the potential for civil unrest and arbitrary detention since a state of emergency was imposed in October 2016. 

The Government of Ethiopia extended the state of emergency on March 15, 2017, and there continue to be reports of unrest, particularly in Gondar and Bahir Dar in Amhara State. This replaces the Travel Warning of December 6, 2016. 
The Government of Ethiopia routinely restricts or shuts downs internet, cellular data, and phone services, impeding the U.S. Embassy’s ability to communicate with U.S. citizens in Ethiopia and limiting the Embassy’s ability to provide consular services. Additionally, the Government of Ethiopia does not inform the U.S. Embassy of detentions or arrests of U.S. citizens in Ethiopia.
Avoid demonstrations and large gatherings, continuously assess your surroundings, and evaluate your personal level of safety. Remember that the government may use force and live fire in response to demonstrations, and that even gatherings intended to be peaceful can be met with a violent response or turn violent without warning. U.S. citizens in Ethiopia should monitor their security situation and have contingency plans in place in case you need to depart suddenly.
Given the state of emergency and the unpredictable security situation, U.S. citizens in Ethiopia should have alternate communication plans in place, and let family and friends know that communication may be limited while you are in Ethiopia. The Department of State strongly advises U.S. citizens to register your mobile number with the U.S. Embassy to receive security information via text or SMS, in addition to enrolling in the Smart Traveler Enrollment Program (STEP).
For further information:
  • See the State Department’s travel website for the Worldwide Caution, Travel Warnings, Travel Alerts, and Country Specific Information for Ethiopia.
  • Enroll in the Smart Traveler Enrollment Program (STEP) to receive security messages and make it easier to locate you in an emergency.
  • Contact the U.S. Embassy in Addis Ababa, located at Entoto Street, P.O. Box 1014, by email at AddisACS@state.gov, or at +251-11-130-6000 Monday-Thursday, 7:30 a.m.-5:00 p.m. For after-hours emergencies, U.S. citizens should call +251-11-130-6911 or 011-130-6000 and ask to speak with the duty officer.
  • Call 1-888-407-4747 toll-free in the United States and Canada or 1-202-501-4444 from other countries from 8:00 a.m. to 8:00 p.m. Eastern Standard Time, Monday through Friday (except U.S. federal holidays).
  • Follow us on Twitter and Facebook.
US Department of State